News

አዋሽ ባንክ በአምቦ ከተማ አዲስ ህንፃ ሊገነባ ነው

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች የራሱን ህንፃ በመገንባት የሚታወቀው አዋሽ ባንክ በአምቦ ከተማ ጠቅላላ የቦታው ስፋት 1,280 ካ.ሜትር ላይ የሚያርፍ እና ከምድር በታች ቤዝመንት ያለው ባለ ሰባት ወለል (G+7) አዲስ ዘመናዊ ህንፃ ለመገንባት የህንፃውን አርክቴክቸራል ዲዛይን ስራ አጠናቋል፡፡ ባንኩ የህንፃውን አርክቴክቸራል ዲዛይን ለማሰራት ባወጣው ጨረታ ተወዳድሮ ላሸነፈው አማካሪ ድርጅትም የእውቅና ሰርቲፍኬት እና የገንዘብ ሽልማት […]

ለክቡራን የአዋሽ ባንክ ባለአክሲዮኖች፣ ደንበኞች እና የአዋሽ ባንክ ማህበረሰብ በሙሉ! እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን! Kabajamtoota Abbootii Aksiyoonaa, Maamiltootaafi Hawaasa Baankii Awaash Hundaaf Baga Gammaddan, Baga Gammanne!

የባንካችን የተከፈለ ካፒታል ብር 10 ቢሊዮን /አስር ቢሊዮን/ ደረሰ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነባር የግል ባንኮች በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሊደርሱበት ይገባል ብሎ ያስቀመጠውን የ5 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል መጠን አዋሽ ባንክ በእጥፍ በመብለጥ የመጀመሪያው የግል ባንክ ሆኗል፡፡ ለዚህም የባንኩን ባለአክሲዮኖች፣ ደንበኞች እና መላውን ሕብረተሰብ በሙሉ ባንኩ ከልብ ያመሰግናል፡፡ አሁንም አስተማማኝ እና መሪ የግል ባንክ […]

የአዋሽ ባንክ የባለአክሲዮኖች 26ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ተካሄደ፡፡

የአዋሽ ባንክ የባለአክሲዮኖች 26ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ተካሂዷል፡፡ በስብሰባውም ላይ የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ዶ/ር ዲባባ አብደታ በተጠናቀቀው የ2020/21 የሂሣብ ዓመት አዋሽ ባንክ በሁሉም የሥራ ዘርፎች አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገቡንና ከግል ባንኮች የመሪነት ሥፍራውን ለተከታታይ ዓመታት ይዞ መቀጠሉን አስረድተዋል፡፡ በባንኩም የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ መሠረት እ.ኤ.አ. […]

አዋሽ ባንክ ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

በመግባቢያ ሰነዱ ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው አዋሽ ባንክ የፋይናንስ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግና የኤቲኤም የክፍያ ማሽን ተከላ ለማድረግ በሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ከኮርፖሬሽኑ ጋር በትብብር ከመስራቱም ባሻገር የኮርፖሬሽኑን ሰራተኞች የደሞዝ ክፍያ በባንኩ በኩል ተፈጻሚ እንዲሆንና ሌሎችም በርካታ ነጥቦች ይገኙበታል፡፡

Page 9 of 10
1 7 8 9 10

Jul 26, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
57.4895 58.6393
GBP
70.6759 72.0894
EUR
62.3359 63.5826
AED
14.1646 14.4479
SAR
13.8682 14.1456
CHF
62.5028 63.7529

Exchange Rate
Close