አዋሽ ባንክ የደንበኞች ሳምንትን በማክበር ላይ ይገኛል
አዋሽ ባንክ “ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን’’ በሚል መሪ ቃል ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የደንበኞች ሳምንት ከዛሬ የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በዋናው መስሪያ ቤት እና በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በደማቅ ሁኔታ ማክበር ጀምሯል፡፡ የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው በመርሃ-ግበሩ ማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት ባንኩ ከምስረታው ጊዜ ጀምሮ የደንበኞቹን ፍላጐት ለማርካት ደንበኞችን ማዕከል ያደረጉ […]
Happening Now!
የአዋሽ ባንክ የሥራ አመራር አባላት እ.ኤ.አ. የ2025/26 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በማካሄድ ላይ ይገኛሉ::
አዋሽ ባንክ ታሪካዊ የሆነውን 1000ኛ ቅርንጫፉን አስመረቀ
በግል ባንክ ኢንዱስትሪ ፈር ቀዳጅ በመሆን በአምስት ቅርንጫፎች ስራ የጀመረው አዋሽባንክ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ ኤጀርሰ ጎሮ ከተማ1000ኛ ቅርንጫፉን የባንካችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራውን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት አካላት እና እንግዶችበተገኙበት በይፋ አስመርቋል።አዋሽ ባንክ በመላ አገሪቱ ቅርንጫፎቹን በማስፋፋት ህብረተሰቡ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችንበአቅራቢያው እንዲያገኝ […]
“ክብራችን ወገናችን – ደስታችን ማካፈላችን” አዋሽ ባንክ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከአምስት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ድጋፍ አደረገ
አዋሽ ባንክ የ2018 ዓ.ም የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ውስጥ ለሚገኙ አረጋዊያን እና አቅመ-ደካማ ወገኖች የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ። ባንኩ በዘንድሮ የገና በዓል “ክብራችን ወገናችን – ደስታችን ማካፈላችን” በሚል መሪ ቃል ለወገኖቻችን ድጋፍ በማድረግ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን ዳግም ያረጋገጠ ሲሆን፣ በዛሬው እለትም የአዋሽ ባንክ ሲኒየር ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር አቶ ዮሐንስ መርጋ […]
አዋሽ ካፒታል አ.ማ. የካፒታል ገበያ ማዕቀፍ በይፋ ሥራ ጀመረ
የማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዋሽ ካፒታል አ.ማ. የቦርድ ሰብሳቢ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በተናገሩት መሰረት ሀገራችን በፋይናንስ ዘርፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አዲስ ምዕራፍ በመግባት ዘርፈ ብዙ ለውጦችን እያደረገች በምትገኝበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቋቋሙ ለቢዝነስ ዘርፉ ትልቅ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡ የአዋሽ ባንክ ተቀጥላ ኩባንያ የሆነው አዋሽ […]
አዋሽ ባንክ 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አከበረ
አዋሽ ባንክ 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሠራር!” በሚል መሪ ሃሳብ ለባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራር የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል አካሄዷል፡፡መርሐ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የባንኩ ሲኒየር ቺፍ ሆልሴል ባንኪንግ ኦፊሰር እና የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ታደሰ ገመዳ እንደገለፁት ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የትዉልድ ሥነ ምግባር ግንባታ […]
















