624+ ቢሊዮን ብር የሀብት ከፍታ!

በ5 ቅርንጫፎችና በ137 ሠራተኞች የኢትዮጵያ የግል ባንክ ኢንዱስትሪውን አንድ ብሎ ስራ የጀመረው አዋሽ ባንክ፣ በዘመን ፍሰት ውስጥ ሰርክ በስኬት እየፈካ ላለፉት 32 ዓመታት የስኬት ጉዞው ዛሬ ከ1,010 በላይ ቅርንጫፎችና ከ20,658 በላይ ሠራተኞች ያሉት ግዙፍ ተቋም ሆኗል።
ስለዚህ ግዙፍ ተቋም  የ2025/26 ሂሳብ ዓመት የስኬት ጉዞ ቁጥሮች ምን ይላሉ?
📌 624 ቢሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ሀብት።
📌 ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ካፒታል።
📌 84.6 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ።
📌 469.3 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ።
📌 274.1 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር መጠን።
📌 2.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ግኝት።
📌 38.3 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ።
📌 15.77 ቢሊዮን ብር የገቢ ግብር ክፍያ።
📌 ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ለማኅበራዊ ኃላፊነት የተደረገ ድጋፍ። ለመሆኑ ለዚህ ስኬታማ ውጤቱ ምን አገኘ? በግሎባል ፋይናንስ መጽሔት የኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመባል ለ5 ተከታታይ ጊዜያት እንዲሁም የWSBI-ESBG (SDGs) ሽልማትን ለ2ኛ ጊዜ በማግኘት አለም አቀፍ እውቅናውን ተጎናፀፈ።
ይህ ሀሉ የተገለፀው በዛሬው ዕለት በስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የአዋሽ ባንክ የባለአክሲዮኖች 31ኛው መደበኛ እና 19ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ክቡር አቶ ጉሬ ኩምሳ የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው፡፡

ለነዚህ ሁሉ ስኬቶች መመዝገብ  የክቡራን ደንበኞቻችን እምነትና ተሳትፎ፣ የሠራተኞቻችን ትጋትና ቁርጠኝነት፣ እንዲሁም
የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የስራ አመራር አባላት የበሰለ አመራር፣ ድጋፍና ክትትል በጥምረት የፈጠሩት የጋራ ውጤቶች ናቸው። ለዚህ ታላቅ ጉዞ ለነበራችሁ  አበርክቶ  ሁላችሁም ምስጋና ይገባችኀል ብለዋል
አዋሽ ባንክ!

Loading exchange rates...