ለሰባተኛው ዙር መርሐ ግብር የተዘጋጁት የሽልማት ዓይነቶች በሶስት ደረጃዎች የተከፋፈሉ ሲሆኑ ለአንደኛው ዕጣ የተዘጋጀው የሽልማት ዓይነት ብር 1,400,000. 00 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ) የሚያወጣ አንድ አይሱዙ ዘመናዊ የጭነት መኪና ፣ ለሁለተኛ ዕጣ (ስድስት ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው 32 ኢንች ኤልኢዲ ቴሌቪዥኖች እና ለሶስተኛ ዕጣ (ሃያ ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው ስማርት የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ናቸው፡፡
በዚህ መሰረት ወ/ሮ ስምረት ታደሰ ከበደ ከአዲስ አበባ በካዛንቺስ ቅርንጫፋችን የተላከላቸውን የውጭ ምንዛሪ ተቀብለው አሸናፊ ሆነዋል፡፡
ባንካችን መርሓ ግብሩን በተጠናከረ ሁኔታ በማስቀጠል ከታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ስምንተኛውን ዙር ከአዋሽ ይቀበሉ ያሸንፉ ፕሮግራሙን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
[Best_Wordpress_Gallery id=”51″ gal_title=”7th lottery Award”]