የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የሚታወቀው አዋሽ ባንክ ባለፈው ዓመት 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ባከበረበት ወቅት ለተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የብር አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ የገንዘብ ድጋፍ ያገኘው የካናዳ የክርስቲያን ህፃናት ፈንድ የተሰኘ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱም ከባንኩ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ከኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ህፃናት መማሪያ የሚውል የመማሪያ ክፍሎችን ከዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶች፣ ከህፃናት መጫወቻዎችና ከመጠጥ ውሃ ጋር በመገንባት ለህብረተሰቡ ያስረከበ ሲሆን ብሎኩንም በአዋሽ ባንክ ስም ሰይሟል፡፡ ትምህርት ቤቱም በመጪው ሐሙስ የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ይመረቃል፡፡