በመላው የአገሪቱ ክፍሎች ለደንበኞቹ ቀልጣፋ፣ የተሟላና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው ባንካችን አገልግሎቱን በተሻለ ደረጃ ለመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን እስከ ዛሬ ድረስ በሁሉም ቅርንጫፎች በመስኮት ደረጃ ይሰጥ የነበረውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልገሎትን አሁን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎችን በመክፈት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ መሠረት ይህን ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ኢክኽላስ ብሎ በመሰየም (ብራንድ በማድረግ) እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ብቻ የሚሰጡ በአዲስ አበባ ከተማ አራት ቅርንጫፎች፣ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ ራፉ ከተማ፣ በጅግጅጋ እና በጅማ ከተማ በመክፈት የተሟላ የባንክ አገለግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡