አዋሽ ባንክ የካቲት 27 ቀን 2012 ዓ.ም ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጥ ቅርንጫፍ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት፣ በሐላባ ከተማ ‘አማና’ ተብሎ የተሰየመውን የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ብቻ የሚሰጥ ቅርንጫፍ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድረጓል፡፡

በመላው የአገሪቱ ክፍሎች ለደንበኞቹ ቀልጣፋ፣ የተሟላና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው ባንካችን አገልግሎቱን በተሻለ ደረጃ ለመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን እስከ ዛሬ ድረስ በሁሉም ቅርንጫፎች በመስኮት ደረጃ ይሰጥ የነበረውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልገሎትን አሁን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎችን በመክፈት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ መሠረት ይህን ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ኢክኽላስ ብሎ በመሰየም (ብራንድ በማድረግ) እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ብቻ የሚሰጡ በአዲስ አበባ ከተማ አራት ቅርንጫፎች፣ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ ራፉ ከተማ፣ በጅግጅጋ እና በጅማ ከተማ በመክፈት የተሟላ የባንክ አገለግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Apr 19, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.8204 57.9568
GBP
67.6774 69.0309
EUR
60.6615 61.8747
AED
13.9997 14.2797
SAR
13.7079 13.9821
CHF
59.7024 60.8964

Exchange Rate
Close