አዋሽ ባንክ የካቲት 12 ቀን 2012 ዓ.ም የደቡብ ምዕራብ የአገራችን ክፍል ፈርጥ በሆነችውና በንግድ መዳረሻነቷ በምትታወቀው ጥንታዊቷ የጅማ ከተማ ‘ሂራ’ ተብሎ የተሰየመውን የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ብቻ የሚሰጥ ቅርንጫፍ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድረጓል፡

በመላው የአገሪቱ ክፍሎች ለደንበኞቹ ቀልጣፋ፣ የተሟላና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው ባንካችን አገልግሎቱን በተሻለ ደረጃ ለመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን እስከ ዛሬ ድረስ በሁሉም ቅርንጫፎች በመስኮት ደረጃ ይሰጥ የነበረውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልገሎትን አሁን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎችን በመክፈት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ መሠረት ይህን ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ኢክኽላስ ብሎ በመሰየም (ብራንድ በማድረግ) እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ብቻ የሚሰጡ አራት ቅርንጫፎችን በአዲስ አበባ ከተማ በመክፈት የተሟላ የባንክ አገለግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም በምስራቁ የአገራችን ክፍልም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ ራፉ ከተማ እና በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ለአገልገሎት አብቅቷል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Apr 26, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.8903 58.0281
GBP
67.9672 69.3265
EUR
60.9864 69.3265
AED
14.0174 14.2977
SAR
13.7269 14.0014
CHF
59.4683 60.6576

Exchange Rate
Close