አዋሽ ባንክ እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ኮርፖሬሽን በቀጣይ ጊዜያት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዱቃን ደበበ ሲሆኑ ስምምነቱ በርካታ ስራዎችን በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑን የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች ከፊርማ ሥነ ሥርዓቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል ፡፡