የአዋሽ ባንክ የባለአክሲዮኖች 26ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ተካሄደ፡፡

የአዋሽ ባንክ የባለአክሲዮኖች 26ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ተካሂዷል፡፡ በስብሰባውም ላይ የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ዶ/ር ዲባባ አብደታ በተጠናቀቀው የ2020/21 የሂሣብ ዓመት አዋሽ ባንክ በሁሉም የሥራ ዘርፎች አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገቡንና ከግል ባንኮች የመሪነት ሥፍራውን ለተከታታይ ዓመታት ይዞ መቀጠሉን አስረድተዋል፡፡ በባንኩም የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ መሠረት እ.ኤ.አ. 2025 መጨረሻ ላይ ከአሥር ምርጥ የምሥራቅ አፍሪካ ባንኮች መካከል አንዱ ለመሆን ያስቀመጠውን ግብ በተሳካ ሁኔታ እያሳካ መሆኑን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡
ባንኩ ይህንን አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ የቻለው በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ ደረጃ የተደቀኑበትን ፈተናዎች ሁሉ ተቋቁሞ ስለሆነ ለዚህ ውጤት ያበቁትን አካላት ማለትም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን፣ የሥራ አመራር አባላትንና ሠራተኞችን፣ ባለአክሲዮኖችን፣ ደንበኞችን፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑትን አካላት ሁሉ አመስግነዋል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Jul 26, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
57.4895 58.6393
GBP
70.6759 72.0894
EUR
62.3359 63.5826
AED
14.1646 14.4479
SAR
13.8682 14.1456
CHF
62.5028 63.7529

Exchange Rate
Close