የአዋሽ ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት እ.ኤ.አ. የ2020/21 የሥራ አፈፃፀምና የቀጣይ በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በአዲስ አበባ ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል አካሂደዋል ፡፡
አዋሽ ባንክ ከሐምሌ 16 -17 ቀን 2013 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ባካሄደው የሥራ አመራር አባላት ጉባኤ በተጠናቀቀው በበጀት ዓመቱ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ቀጠና ጽ/ቤቶች እንዲሁም ሥራ አስኪያጆች የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት በማበርከት ጉባኤውን አጠናቅዋል ፡፡