አዋሽ ባንክ ጥር 28 ቀን 2012 ዓ.ም የ7ኛው ዙር “ከአዋሽ ይቀበሉ ይሸለሙ” የሎተሪ መርሐ ግብር አሸናፊ ለሆኑ እድለኞች ያዘጋጀዉን ሽልማት ሰጠ፡፡

ለሰባተኛው ዙር መርሐ ግብር የተዘጋጁት የሽልማት ዓይነቶች በሶስት ደረጃዎች የተከፋፈሉ ሲሆኑ ለአንደኛው ዕጣ የተዘጋጀው የሽልማት ዓይነት ብር 1,400,000. 00 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ) የሚያወጣ አንድ አይሱዙ ዘመናዊ የጭነት መኪና ፣ ለሁለተኛ ዕጣ (ስድስት ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው 32 ኢንች ኤልኢዲ ቴሌቪዥኖች እና ለሶስተኛ ዕጣ (ሃያ ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው ስማርት የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ናቸው፡፡

በዚህ መሰረት ወ/ሮ ስምረት ታደሰ ከበደ ከአዲስ አበባ በካዛንቺስ ቅርንጫፋችን የተላከላቸውን የውጭ ምንዛሪ ተቀብለው አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ባንካችን መርሓ ግብሩን በተጠናከረ ሁኔታ በማስቀጠል ከታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ስምንተኛውን ዙር ከአዋሽ ይቀበሉ ያሸንፉ ፕሮግራሙን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡

[Best_Wordpress_Gallery id=”51″ gal_title=”7th lottery Award”]

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Nov 12, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
120.3227 122.7291
GBP
147.9211 150.8796
EUR
130.4656 133.0749
AED
29.6462 30.2391
SAR
29.0254 29.6059
CHF
130.8152 133.4315

Exchange Rate
Close