አዋሽ ባንክ የካናዳ ክርስቲያን ህፃናት ፈንድ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በአዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ህፃናት የተሟላ የመጠጥ ውሃና ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች እንዲሁም የህፃናት መጫወቻዎች ያሏቸው የመማሪያ ክፍሎችን አስገነባ፡፡

የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የሚታወቀው አዋሽ ባንክ ባለፈው ዓመት 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ባከበረበት ወቅት ለተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የብር አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ የገንዘብ ድጋፍ ያገኘው የካናዳ የክርስቲያን ህፃናት ፈንድ የተሰኘ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱም ከባንኩ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ከኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ህፃናት መማሪያ የሚውል የመማሪያ ክፍሎችን ከዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶች፣ ከህፃናት መጫወቻዎችና ከመጠጥ ውሃ ጋር በመገንባት ለህብረተሰቡ ያስረከበ ሲሆን ብሎኩንም በአዋሽ ባንክ ስም ሰይሟል፡፡ ትምህርት ቤቱም በመጪው ሐሙስ የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ይመረቃል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Apr 18, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.8022 57.9382
GBP
67.5744 68.9259
EUR
60.4375 61.6463
AED
13.9956 14.2755
SAR
13.7039 13.9780
CHF
59.5391 60.7299

Exchange Rate
Close