አዋሽ ባንክ ከሬይስ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

አዋሽ ባንክ ከሬይስ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው እና  የሬይስ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዲአዚዝ ሀሰን ሲሆኑ ስምምነቱ በርካታ የፋይናንስ ስራዎችን በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑን የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡የመግባቢያ ስምምነቱ ዋና ዓላማ ባንኩ ተደራሽነቱን በማስፋት እንዲሁም ከሬይስ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር ማይክሮ ፋይናንሱ በሰፊው በሚንቀሳቀስባቸው በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል ለሚገኙና የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ላልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ በቴክኖሎጂ የታገዘ አስተማማኝ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት እንደሆነም ተጠቁሟል።

አዋሽ ባንክ በምስራቅ የሀገራችን ክፍል ማለትም በድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ እንዲሁም በቶጎጫሌ አካባቢ በቀዳሚነት ቅርንጫፎቹን የከፈተ የመጀመሪያው የግል ባንክ ነው፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Nov 28, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
55.6854 56.7991
GBP
67.1870 68.5307
EUR
60.9588 62.1780
AED
13.7216 13.9960
SAR
13.4363 13.7050
CHF
60.3764 61.5839

Exchange Rate
Close