አዋሽ ባንክ የመጋዘን ደረሰኝ የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል

የመጋዘን ደረሰኝ ብድር አንድ አምራች ወይም ተገበያይ ምርቱን ወደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ መጋዘን በማስገባትና የመጋዘን ደረሰኙን (WR) እንደ ማስያዣ በመጠቀም የሚያገኝ የብድር አገልግሎት ነው፡፡በዚህ መሰረት ተበዳሪው አርሶ አደር፣ የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየኖች እና አቅራቢዎች መያዣ እንዲሆን ካስገብት ምርት ውጭ ሌላ ንብረት ለመያዣነት ሳያስፈልጋቸው ከባንክ የአጭር ጊዜ የብድር አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
በዚሁ መሰረት አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ የምርት ገበያ ድርጅት ጋር በመተባበር ለድርጅቱ ደንበኞች የአጭር ጊዜ ብድር አገልግሎት ማቅረብ የጀመረ ሲሆን ይህንን የብድር አገልግሎት የሚሰጠው በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት እንዲገበያዩና በድርጅቱ መጋዘኖች እንዲከማቹ ለተፈቀደ የግብርና ምርቶች ነው፡፡ የብድር አገልግሎቱን ለማግኝት አምራቾቹ ባንኩ በብድር ፖሊሲው ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው መገኘት አለባቸው፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

May 02, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.9239 58.0624
GBP
68.1921 69.5559
EUR
61.0167 62.2370
AED
14.0245 14.3050
SAR
13.7344 14.0091
CHF
59.5882 60.7800

Exchange Rate
Close