አዋሽ ባንክ ዘመናዊ የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ ከማድረጉም ባሻገር በተለያዩ ግዜያት የኮርፖሬት ማህበራዊ ግዴታውን በሚገባ በመወጣት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀን አንድ ጊዜ እንኳን መመገብ የማይችሉ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርገውና ተስፋ ብርሃን የተሰኘውን የምገባ ማዕከል አስገንብቷል።
በልደታ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ይህ የምገባ ማዕከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በተገኙበት ዛሬ በይፋ ስራ የጀመረ ሲሆን በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከሉን አዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ ብለው ሰይመውታል።