አዋሽ ባንክ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ 50 ሺህ ችግኞችን በመትከል አረንገጓዴ አሻራቸውን አኖሩ::

እህት ኩባንያዎቹ አዋሽ ባንክ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን በሰበታ ሐዋስ ወረዳ በደበል ዮሐንስ ተራራ ከወረዳው የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር 20 ሺህ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በፕሮግራሙ ላይ በዳረጉት ንግግር እህት ኩባንያዎቹ አዋሽ ባንክና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ባለፉት 26 ዓመታት ውስጥ በሀገራችን የልማትና የምጣኔ ሀብት ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ካስቀመጡት የግል የፋይናንስ ተቋማት መካከል ግንባር ቀደም ከመሆናቸውም በተጨማሪ ለአገሪቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ትልቅ ተሳትፎ ሲያደርጉ የቆዩና አሁንም እያደረጉ ያሉ መሆናቸውን  አስታውቀዋል፡፡

ባለፈው ዓመት የጠቅላይ ሚኒስትራችንን የአረንጓዴ አሻራ ጥሪ በመቀበልና  25ኛ ዓመት የምስረታ በዓላቸውን ምክንያት በማድረግ ሐምሌ 13 ቀን 2011 ዓ.ም በእንጦጦ ተራራ የሁለቱን እህት ኩባንያዎች ሰራተኞች በማስተባበር አስር ሺህ ችግኞችን በመትከል አሻራችንን አኑረናል ያሉት አቶ ፀሐይ እህት ኩባንያዎቹ  የቆየ ልምድ ያላቸው  ሲሆን ከዚህ  በፊት በተለያዩ አካባቢዎች የተከሏቸውና በዚህ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩት አካላት ባደረጉት ድጋፍ የተተከሉ ችግኞች ዛሬ ላይ ወደ ደንነት ተለውጠው የአከባቢውን የተፈጥሮ ሚዛን ከማስጠበቅ አንፃር ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከት ችለዋልም ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ከኢትዮጵያ ተፈጥሮና የቅርስ ጥበቃ ባለአደራ ማህበር ጋር በመተባበበር በእንጦጦ ተራራ የተተከሉ ችግኞችም እህት ኩባንያዎቹ ለጥበቃና እንክብካቤአቸው በቂ በጀት በመመደባቸው ከ70 በመቶ በላይ ፀድቀው በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮ ዓመትም ባለፈው ዓመት “አንድ ሰው አርባ ችግኝ በሚል” በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለማስቀጠል በዚህ ዓመትም እህት  ኩባንያዎቹ “የአዋሾች የአረንጓዴ አሻራ ቀን” በሚል መሪ ቃል በጋራ በመሆን በአገር አቀፍ ደረÍ እስከ 50 ሺህ ችግኞችን ለመትከል አቅደዋል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው  ከእነዚህም ውስጥ ከሰበታ ሐዋስ እርሻና የተፈጥሮ ሀብት ፅ/ቤት ጋር በመተባበበር በሁለት ሄክታር መሬት ላይ የሚተከሉ ሃያ ሺህ ችግኞች የዘመቻው ዋነኛው አካል መሆኑን የገለፁት አቶ ፀሐይ  በተመሳሳይ ሁኔታ በዛሬው ዕለትና በሚቀጥሉት ቀናት በሁሉም የአገራችን ክፍሎች የሚገኙ የቀጠና ፅ/ቤቶችና የቅርንጫፍ ሰራተኞቻችንም ባሉበት አካበቢ ካሉት የመንግስት መዋቅሮች ጋር በመቀናጅትና ሰራተኞቻቸውን በማስተባበር ሰላሳ ሺህ ችግኞችን እንደሚተክሉም አስታውቀዋል፡፡

የዘንድሮውን የችግኝ ተከላን ከወትሮው ለየት የሚያደርገው ለእህት ኩባንያዎቻችን ስያሜ መነሻ የሆነውና የአገራቸን የልማት አጋር በሆነው የአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ ላይ የሚካሄድ እንደመሆኑ መጠን ለአዋሽ ወንዛችን የሚደረገው ጥበቃ አካል ተደርጎ ሊታይ የሚችል መሆኑ ነው ብለዋል አቶ ፀሐይ፡፡ከዚህም በተጨማሪ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በጉድጓድ ዝግጅት፣  በተከላና በቀጣይነት በሚሰራው የጥበቃና እንክብካቤ ስራ ለአከባቢው ወጣቶች የስራ ዕድል እና በወረዳው በችግኝ አምራችነትና ሽያጭ ለተደራጁ ወጣቶችም የገበያ ዕድል ለመፍጠር መቻሉንም ገልፀዋል፡፡

የአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጉዲሳ ለገሰ በበኩላቸው የ2012 ዓ.ም የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ዓላማ እህት ኩባንያዎቹ አዋሽ ባንክና አዋሽ ኢንሹራንስ ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር ያለባቸውን ተቋማዊ ማህበራዊ ኃላፊነት በመወጣት በደኖች መመናመን አማካይነት ሊመጣ የሚችለውን የአየር ንብረት ለውጥና ተጓዳኝ ችግሮችን ከመቋቋም አንፃር ለተነደፈው አገራዊ ፖሊሲ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት መሆኑን ገልፀው የአካባቢው ህብረተሰብም ይህንኑን ተረድቶ ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ አንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

እህት ኩባንያዎቹ ለተከሏቸው ችግኞች አስፈላጊውን በጀት በመመደብ ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ እያደረጉላቸው በተፈለገው መልኩ አድገው የአካባቢያችንና የአገራችንን ተፈጥሯዊ ሚዛን በማስጠበቅ ውስጥ ድርሻ እንዲኖራቸው እነደሚያደርጉ አቶ ጉዲሳ አረጋግጠዋል፡፡

 

 

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Jan 02, 2025 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
124.7041 127.1982
GBP
153.3074 156.3736
EUR
135.2163 137.9206
AED
30.7258 31.3403
SAR
30.0824 30.6841
CHF
135.5787 138.2902