አዋሽ ባንክና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በቀጣይ ጊዜያት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የመግባብያ ስምምነቱ ዋና አላማ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካትና ዘመኑን የዋጁ ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ በመስጠት ላይ የሚገኘው አዋሽ ባንክ አዳዲስ የባንኪንግ ቴክኖሎጂዎችን በሃገሪቱ አንጋፋ እና በስርጭት ሽፋኑ ግንባር ቀደም የመንግስት የሚዲያ ተቋም ከሆነው ኢቢሲ ጋር በጋራ በመስራት በሰፊው ለማስተዋወቅና እየሰጠ በሚገኘው የባንኪንግ አገልግሎቶች ላይ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው፡፡
በመሆኑ የመግባቢያ ስምምነቱ ለሁለቱ ተቋማት ለአገራችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጥ አብረውና ተደጋግፈው ለመስራት ምቹ መደላድልን የሚፈጥር ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ስምምነቱ የባንኩ አገልግሎቶች በየጊዜው ለህብረተሰቡ እንዲደርሱና ህብረተሰቡም የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል ነው፡፡ እንደዚሁም ኢቢሲ አገልግሎቱን ለማዘመንና ተደራሽነቱን ለማስፋፋት የሚያደርገውን ጥረት ባንኩ በሚችለው አቅም ሁሉ እንዲያግዘው ይረዳል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ የተፈረመው በአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ በአቶ ፀሐይ ሽፈራው እና በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ በ ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ ታህሳስ 19 ቀን 2012 ዓ.ም በረመዳ ሆቴል ነበር::

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

May 02, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.9239 58.0624
GBP
68.1921 69.5559
EUR
61.0167 62.2370
AED
14.0245 14.3050
SAR
13.7344 14.0091
CHF
59.5882 60.7800

Exchange Rate
Close