አዋሽ ባንክ በብድር ላይ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔ ዝቅ እንዲል አደረገ::
አዋሽ ባንክ በብድር ላይ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔ ከ 0.5%-4.5% ዝቅ እንዲል አድርጉዋል፡፡ ባንኩ በብድር ላይ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔ ከ 0.5% – 4.5% ዝቅ እንዲል ያደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች፡-
1. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቦንድ ግዥ መመሪያን ማሻሻሉ አዋሽ ባንክ ለቦንድ ግዥ የሚያውለውን ገንዘብ ለብድር በማዋል ትርፋማነቱን በአስተማማኝ ሁኔታ መቀጠል የሚያስችለው መሆኑ በጥናት በመረጋገገጡ፣
2. በብድር ላይ የሚከፈለው የወለድ ምጣኔ ዝቅ መደረጉ በአገራችን እየታየ ያለውን የዋጋ ግሽበት ለማስተካከል የራሱ የሆነ በጎ ተጽእኖ ይኖረዋል ተብሎ ስለታመነ፣
በአጠቃላይ የወለድ ምጣኔ ማስተካከያው የአገራችንን የኢንቨስትመንት እና የንግድ እንቅስቃሴ በማበረታታት ለአገራችን የኢኮኖሚ መረጋጋት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ይታመናል፡፡
የአዋሽ ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቦንድ ግዥ እ.ኤ.አ ኦክቶበር፣ 2019 መጨረሻ ላይ ብር 12.4 ቢሊዮን ነበር፡፡