አዋሽ ባንክ ከፍተኛ የወለድ ምጣኔ ቅነሳ አደረገ

በአለም ጤና ድርጅት በወረርሽኝነት የተፈረጀው የኮሮና ቫይረስ በዓለማችን ላይ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ መተኪያ የሌለውን የሰው ልጅ ህይወት ከመቅጠፍም አልፎ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ድቀትን አስከትሏል፡፡ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች እንቅስቃሴዎችም ከመቀዛቀዛቸው የተነሳ በዓለማችን ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችም ለስራ አጥነት ተዳርገዋል፡፡

ወረርሽኙ በአገራችን መከሰቱን የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ካሳወቁበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ተፅእኖዎች ቀላል የሚባሉ አይደሉም፡፡ ይህ ወረርሽኝ በንግድ እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት አዋሽ ባንክ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የተለያዩ ማሻሻያዎችን አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድና ማነጅመንት ቫይረሱ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ እያደረሰ ያለውን ተፅእኖ ከገመገመ በኋላ በተለይም የችግሩ ቀጥተኛ ተፅእኖ ሰለባ ለሆኑት አገልግሎት ሰጪ ሴክተሮች ላይ ለተሳማሩት ተበዳሪ ደንበኞቹ ከፍተኛ የወለድ ምጣኔ ቅነሳ አድርጓል፡፡ የወለድ ምጣኔ ቅነሳው የተደረገላቸው የኢኮኖሚ ዘርፎችም የሆቴል እና ቱሪዝም፣ የጉዞና አስጎብኚ ድርጅቶች እና የአበባ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሲሆኑ ለሆቴሎች ቀደም ሲል ከ12.5 እስከ 15.75 በመቶ ፣ ለጉዞና አስጎብኚ ድርጅቶችና ለአባባ አምራቾች ከ 9 እስከ 12.5 በመቶ የነበረው የወለድ ምጣኔ ለቀጣይ ሶስት ወራት ወደ ዝቅተኛው የወለድ ምጣኔ ማለትም ወደ (7%) ሰባት በመቶ እንዲቀንስላቸው ተደርጓል፡፡ ባንኩ ይህንን የወለድ ቅነሳ በማድረጉም በትንሹ እሰከ ብር 50 ሚሊዮን የሚደርስ ገቢ የሚያጣ ይሆናል፡፡

አዋሽ ባንክ የወረርሽኙን በአገራችን መከሰት ተከትሎ ቀደም ሲልም የኤልሲ ማራዘሚያ የኮሚሽን ክፍያ፣ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ለተሰማሩ ተበዳሪዎቹ የብድር መመለሻ ጊዜ ማራዘሚያ የኮሚሽን ክፍያ እና ኤቲኤም ለሚገለገሉ ደንበኞቹ ያስከፍል የነበረውን የአገልግሎት ክፍያ እ.አ.አ ከኤፕሪል 01/2020 ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ወራት ሙሉ በሙሉ ነፃ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Dec 21, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
124.6101 127.1023
GBP
153.1919 156.2557
EUR
135.1144 137.8167
AED
30.7026 31.3167
SAR
30.0597 30.6609
CHF
135.4765 138.1860

Exchange Rate
Close