አዋሽ ባንክ ከጅማ ዩኒቨርስቲ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡ በስምምነቱም አዋሽ ባንክ የቤት መስሪያ፣ የመኪና መግዥያ እና ቢዝነስ ማካሄጃ ብድር በዝቅተኛ ወለድ ለማቅረብና የብድሩን አከፋፈል ሂደት ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ ለማስተዳደር እንዲሁም ሌሎችም በርካታ ነጥቦች ተካተዋል፡፡
አዋሽ ባንክ ቀደም ሲል ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ የልማት ተቋማት ጋር ለመስራት የሚያስችሉትን የመግባቢያ ሰምምነቶችን በመፈራረም ተቋማቱ የሚፈልጉትን የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡