ባንካችን ላለፉት ዓመታት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በመመደብ በበርካታ የልማት፣ የሰብዓዊ ዕርዳታና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተሳትፎ አድርጓል፤ አሁንም በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የአዋሽ ባንክ ባለአክሲዮኖች እና ባንኩን በበላይነት የሚመራው የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ የማህበራዊ ኃላፊነት ግዴታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በየዓመቱ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የሚጠበቅበትን ማህበራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ በማድረግ ባንኩ በህብረተሰቡ ዘንድም ሆነ በየደረጃው ካሉት የመንግስት ተቋማት ዘንድ መልካም ዝናን እንዲያተርፍ አድርገዋል፡፡