የአዋሽ ብር የማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ተካሄደ

በግል የባንክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ፈር ቀዳጅና መሪነቱን አስጠብቆ የቀጠለው እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት ዘመኑን የዋጁ የባንኪንግ አገልግሎቶችን በማቅረብ የሚታወቀው አዋሽ ባንክ ‘‘አዋሽ ብር’’ የተሰኘ የሞባይል መኒ እና የዉክልና ባንክ አገልግሎት የማስጀመሪያ ፕሮግራም የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል በይፋ ተካሂዷል፡፡
በስነ-ስርዓቱ ላይ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው እንደገለጹት ባንኩ በአሁኑ ወቅት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተደራሽ ለመሆን መቻሉን ጠቅሰው፡ ማህበረሰቡ ከቅርንጫፎች በተጨማሪ በቦታና በጊዜ ሳይገደብ በሁሉም ጊዜያትና ቦታዎች የአገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የኤቲኤም፣ የሞባይል ክፍያ ፤ የወኪል አገልግሎት፤የኢንተርኔት ባንኪንግና የፖስ ማሽን የክፍያ ዘዴዎች መቅረባቸውን አስረድተዋል፡፡
የአዋሽ ባንክ ደንበኞች ወይም ተጠቃሚዎች የአዋሽ ብር መተግበሪያን በመጠቀም ወይም የአዋሽ ብር ወኪሎች ጋር በመቅረብ የሚከተሉትን ዋና ዋና አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ፡፡
1. የሂሣብ እንቅስቃሴዎችን መከታተል
2. ገንዘብ ማስተለለፍ
3. ከአዋሽ ብር ወኪሎችና ኤቲኤሞች ገንዘብ ወጪ ማድረግ
4. የተለያዩ ክፍያዎችን መፈጸም (የትራፊክ ቅጣት፣ የአየር መንገድ ትኬት ክፍያ፣ የDSTV፣ የCANAL+፣ የት/ቤት ክፍያዎች ወዘተ) እና
5. የሞባይል ካርድ መሙላት ናቸው፡፡

ደንበኞች ወደ ቅርንጫፎች መሄድ ሳያስፈልጋቸው በአቅራቢያቸው በሚገኙ የአዋሽ ብር ወኪሎች አማካኝነት ሂሣብ መክፈት፣ ገንዘብ ገቢና ወጪ ማድረግ፣ እና ከላይ የተገለጹ አገልግሎቶችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የወኪል ባንክ አገልግሎት እና ሌሎችም አገልግሎቶች እንዲካተቱ ተደርጎ ለደንበኞች በ6 ቋንቋዎች ማለትም በ እንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ በትግርኛ፣ በአፋር እና በሱማሊኛ ቋንቋዎች ለአጠቃቀም ምቹና ቀላል ሆኖ የቀረበ ሲሆን በማንኛውም ዓይነት የስልክ ቀፎዎች ላይ የሚሰራ ነው፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Oct 10, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
111.4816 125.8886
GBP
144.6929 154.7637
EUR
123.9777 136.5008
AED
30.6012 31.0175
SAR
29.9606 30.3682
CHF
127.9601 136.8664

Exchange Rate
Close