አዋሽ ባንክ ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ አተረፈ::

በመጪው ህዳር የብር እዮበልዩውን ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው አዋሽ ባንክ በ2011 የሒሳብ ዓመት ከታክስና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማስመዝገብ ከሌሎች የግል ባንኮች ጋር ያለውን ልዩነት በማስፋት የመሪነት ሚናውን ለአራተኛ ጊዜ አረጋግጧል፡፡

ባንኩ በ2011 የሒሳብ ዓመት ያስመዘገበው የ3,329,766,285 ብር ትርፍን ልዩ የሚያደርገሀው በግል ባንኮች የትርፍ ምጣኔ ከፍተኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በአንድ ዓመት የ1.36 ቢሊዮን ብር ወይም የ70 በመቶ ዕድገት የታየበት መሆኑ ነው፡፡ ባንኩ ባለፈው ዓመት በኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ ተብሎ የተጠቀሰውን ሁለት ቢሊዮን ብር ማትረፉ የሚታወስ ሲሆን በዘንድሮው የሒሳብ ዓመት ያስመዘገበው ትርፍ ግን ከሌሎች የግል ባንኮች ጋር የነበረውን ልዩነት እጅጉን ያሰፋበት ነው፡፡

 የዘንድሮው የሒሳብ ዓመት አዋሽ ባንክ ከፍተኛ ትርፍ በማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ዘርፎችም ማለትም በደንበኞች ቁጥር፣ በተከፈለ ካፒታል፣ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን፣ የባንኩ አስቀማጮች ቁጥርና ባንኩ ሰጠው የብድር መጠን  እንዲሁም በተያያዥ የኢንዱስትሪው መለኪያዎች አንፃር ከግል ባንኮች በቀዳሚነት የሚያስቀምጡት አፈፃፀሞችን ያስመዘገበበትም ነው፡፡ ለዚህም የባንኩ የ2011 የሂሳብ ዓመት የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ62.2 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ አንዱ ማሳያ እንደሆነና ይህም ካለፈው የሂሳብ ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ16.3 ቢሊዮን ብር ወይም የ36 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑን የባንኩ ግርድፍ የሂሳብ ሪፖርት አመልክቷል፡፡ የባንኩ አስቀማጮች ቁጥርም 2.7 ሚሊዮን በላይ መድረሱም ተጠቁሟል፡፡

ባንኩ በ2011 የሂሳብ ዓመት መጨረሻ የሰጠው ብድር ከ47.1 ቢሊዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን ይህም ባለፈው የሂሳብ ዓመት ከሰጠው 15.8 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ51 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ በግርድፍ ሪፖርቱ ላይ እንደተመለከተው የባንኩ ዓመታዊ ገቢም  ከ5.4 ቢሊዮን ብር ወደ ስምንት ቢሊዮን ብር በማደግ  ካለፈው ዓመት የ2.5 ቢሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል፡፡  የባንኩ የተከፈለው የካፒታል መጠንም የ49 በመቶ ዕድገት በማሳየት ከ4.3 ቢሊዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን  ይህም ከግል ባንኮች የመጀመርያውን ደረጃ እንዲይዝ አድርጎታል፡፡ ባንኩ በ2011 የሂሳብ ዓመት 2.6 ቢሊዮን ብር ለማትረፍ አቅዶ ነው ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ ያተረፈው፡፡ የተመዘገበው አመርቂ ውጤት የሁሉም ሰራተኞችና የባንኩ አነመራሮች ድምር ውጤት መሆኑን እውቅና በመስጠት የባንኩ የዳሬክተሮች ቦርድ ለባንኩ ሰራተኞችና አመራሮች የሶስት ወር ደመወዝ በማትጊያነት በማበርከት የሶስት እርከን የደመወዝ ጭማርን ፈቅዷል፡፡ 

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Jul 26, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
57.4895 58.6393
GBP
70.6759 72.0894
EUR
62.3359 63.5826
AED
14.1646 14.4479
SAR
13.8682 14.1456
CHF
62.5028 63.7529

Exchange Rate
Close