አዋሽ ባንክ የኢፍጣር መርሐ-ግብር አካሄደ።

አዋሽ ባንክ የታላቁ የረመዳን ወርን በማስመልከት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም ምኞቱን ለመግለጽና ለደንበኞቹ ያለውን አጋርነት ለማረጋገጥ በማሰብ በ ቀን 11,2014 ዓ.ም  በሸራተን አዲስ ሆቴል የጋራ የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት ያካሄደ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ባንኩ የሸሪአ መርሆችን መሰረት አድርጎ በማቅረብ ላይ በሚገኘው ‘’አዋሽ ኢኽላስ’’ የተሟላ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶች በተጨማሪ ኢጃራ ፋይናንሲንግ፣ ቃርዱል ሀሰን ፋይናንሲንግ እንዲሁም አል- ከይር ዋድያ (የተቀማጭ ሂሳብ) የተሰኙ አዳዲስ ፕሮዳክቶችን በይፋ አስጀምሯል፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራውን ጨምሮ ፣ የአዋሽ ባንክ የሸሪዓ አማካሪዎች ፣ የባንኩ የሥራ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ ባንኩ በሸሪዓ መርሆች ላይ የተመሰረተውን የአዋሽ ኢኽላስ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዓይነቶችና ተደራሽነት ለማስፋት ጠንክሮ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Apr 25, 2025 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling