አዋሽ ባንክ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችን ሸለመ

አዋሽ ባንክ እ.ኤ.አ በ2018/19 የሂሳብ ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች እና ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እውቅና እና ሽልማት ሰጠ፡፡ ባንኩ ሽልማቱን የሰጠው ሐምሌ 29 እና 30 2011 ዓ.ም ባካሄደው ዓመታዊ የስራ አመራሮች ስብሳባ መጨረሻ ላይ ሲሆን ተሸላሚዎቹ ቅርንጫፎችም በሂሳብ ዓመቱ ባስመዘገቡት ከፍተኛ ትርፍና በሐዋላ አገልግሎት በርካታ ደንበኞችን በማስተናገድ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት የተመረጡ ናቸው፡፡
ቅርንጫፎቹ ካስመዘገቡት አመርቂ ውጤት ጀርባ ቅርንጫፎቹን በቅርበት በማገዝ፣ በመከታተል፣ አቅጣጫ በመጠቆም፣ አዳዲስ ደንበኞችን በመመልመልና ነባር ደንበኞችን በመጎብኘት፣ መልካም ተሞክሮዎችን በማጋራት አቅም ግንባታው ላይ በመስራትና የተለያዩ ድጋፎችን ያደረጉ የቀጠና ስራአስኪያጆችም በዚሁ ፕሮግራም ላይ ምስጋናና ሽልማት ተችረዋል፡፡
ተሸላሚ ቅርንጫፎቹ እንዳስመዘገቡት ውጤት ዋንጫና የምስክር ወረቀት የተሸለሙ ሲሆን የተሸለሚ ቅርንጫፎችና ቀጠናዎች ስራ አስኪያጆችም የአንድ አንድ ወር ደመወዝ ተጨማሪ ቦነስ እና የአንድ አንድ እርከን ተጨማሪ የደመወዝ ጭማሪ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት 23 ቅርንጫፍ አራት ቀጠና ስራ አስኪያጆችን ለማበረታታት ለአጭር ጊዜ ስልጠና ወደ ውጭ አገር እንደሚላኩም የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ አሳውቀዋል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Jun 07, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
54.3747 55.4622
GBP
64.4580 65.7472
EUR
58.1483 59.3113
AED
13.3964 13.6643
SAR
13.1217 13.3841
CHF
57.2144 58.3587

Exchange Rate
Close