አዋሽ ባንክ ከዘጠኝ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት ጋር የብድር አቅርቦት ስምምነት አደረገ

አዋሽ ባንክ መካከለኛ፣ አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ ከዘጠኝ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት ጋር የብድር አቅርቦት ስምምነት አድርጓል፡፡ ባንኩ ይህን ስምምነት ያደረገው ዘጠኙ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋማትም፦ ቪዥን ፈንድ፣ ንስር፣ ቀንዲል፣ መተማመን፣ መክሊት፣ ዳይናሚክ፣ ዋሳሳ፣ ሃርቡ እና ፒስ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም ይገኙበታል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የስራና ክህሎት ምኒስቴር ምኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈርሃት ካሚል እንደተናገሩት የመካከለኛ፣ አነስተኛና ጥቃቅን የሥራ ዘርፎች ለሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ ለኢኮኖሚ ዕድገት እና ለማህበራዊ ችግሮች ማቃለያ ከፍተኛ ሚና ቢኖራቸውም ያላቸውን እምቅ አቅም ተጠቅመው ወደ ሥራ ለመግባት የፋይናንስ አቅርቦት ውስንነት እንዳለባቸው በመግለፅ ባንኩ ላደረገው የብድር ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ሌሎች የፋይናንስ ተቋማትም ለዘርፉ እድገት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Mar 24, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
53.8704 54.9478
GBP
63.2737 64.5392
EUR
58.5841 59.7558
AED
13.2733 13.5388
SAR
12.9782 13.2378
CHF
56.1456 57.2685

Exchange Rate
Close