አዋሽ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችን በተለያዩ አካባቢዎች በመክፈት ላይ ነው::

አዋሽ ባንክ ቀደም ሲል በሁሉም ቅርንጫፎቹ በመስኮት ደረጃ ብቻ ይሰጥ የነበረውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እራሱን አስችሎ በቅርንጫፍ ደረጃ መስጠት ጀምሯል፡፡ እስካሁን ድረስ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች 11 ያህል አዳዲስ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎችን ከፍቶ የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ሰዓት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት ርንጫፎችም፡-
1.ሙዓመላት ቅርንጫፍ- አዲስ አበባ ቤቴል አካባቢ
2.ክህድማ ቅርንጫፍ- አዲስ አበባ ተክለሃይማኖት በርበሬ በረንዳ አካባቢ
3.ሰባተኛ- አዲስ አበባ ሰባተኛ ድሬ ህንፃ ላይ
4.ቦሌ ሚካኤል – አዲስ አበባ አዋሽ ባንክ ቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፍ ያለበት ህንፃ ላይ
5.አመል ቅርንጫፍ – አዲስ አበባ መርካቶ አውቶብስ ተራ
6.ሁዳ ቅርንጫፍ – ምስራቅ ሀረርጌ መልካራፉ ከተማ
7.በርዋቆ ቅርንጫፍ – ጅግጅጋ ከተማ
8.ሂራ ቅርንጫፍ – ጅማ ከተማ አዋሽ ባነክ ህንፃ ላይ
9.በረካ ቅርንጫፍ- ሻሸመኔ ከተማ ሐላባ ማዞሪያ ላይ
10.አማና ቅርንጫፍ- ሐላባ ከተማ
11.ናፍኢ ቅርንጫፍ- ነቀምቴ ከተማ ሲሆኑ በቅርቡም በባሌ ሮቤ፣ በድሬዳዋ፣ በደሴ እና
በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በተለያዩ ከተሞች ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በመክፈት አገለግሎቱን በስፋት የማዳረስ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Jun 08, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
54.3861 55.4738
GBP
64.6741 65.9676
EUR
58.2693 59.4347

Exchange Rate
Close