አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አቢያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ::

(ጥር 03 ቀን 2013 ዓ.ም አዋሽ ባንክ፣ አዲስ አበባ) አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አቢያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው እና የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አቢያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዝዳንት እያሱ ኤልያስ (ዶ/ር) ሲሆኑ በስምምነቱ ላይ ለእምነት ተቋማት ልዩ ትኩረት በመስጠት በርካታ የፋይናንስና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ እንዲሁም በተመረጡ የልማት ዘርፎች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑን የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡
አዋሽ ባንክ የመንግስትን አቅጣጫ በመከተል ከበርካታ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነቶች በማድረግ ላይ ሲሆን በዚህም በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛል።
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አቢያተ ክርስቲያናት ካውንስል በስሩ ከሰላሳ ሚሊዮን በላይ አባላትን ይዞ እንዲሁም ከሰላሳ አምስት ሺህ በላይ ቤተ-እምነቶችን በማቀፍ ከተመሰረተ ጥቂት ወራትን ያስቆጠረ ቢሆንም የጎልማሳ ራዕይን ሰንቆና ሀገራዊ ፋይዳውን በማሳደግ እንዲሁም አፍሪካንና ዓለም ዓቀፍ ገጽታን በመገንባት ከመንቀሳቀሱም ባሻገር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰፊ የልማት ሥራዎችና የአካባቢ ጥበቃ ላይ በመስራት ላይ የሚገኝ የእምነት ተቋማት ካውንስል ነው።
Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Jul 26, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
57.4895 58.6393
GBP
70.6759 72.0894
EUR
62.3359 63.5826
AED
14.1646 14.4479
SAR
13.8682 14.1456
CHF
62.5028 63.7529

Exchange Rate
Close