አዋሽ ባንክ እ.ኤ.አ. በ2020/21 የሂሣብ ዓመት ብር 5.58 ቢሊዮን ዓመታዊ ትርፍ አስመዘገበ

………………………………………….

ላለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት ከግል ባንኮች የመሪነት ሥፍራውን ይዞ የቆየው አዋሽ ባንክ አሁን በተገባደደው የሂሣብ ዓመትም በዋና ዋና የባንኪንግ ዘርፎች የመሪነት ሥፍራውን ይዞ መቀጠሉን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀው ሂሣብ ዓመት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ የተቀማጭ ሂሣብ መጠን በማስመዝገብ በባንኩም ሆነ በግል ባንኮች ታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን ውጤት አስመዝግቧል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ሂሣብ ኤልሲ ማርጅንን ጨምሮ ብር 107.7 ቢሊዮን ሲሆን፣ ይህም አሀዝ ከባለፈው ሂሣብ ዓመት ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የብር 33.8 ቢሊዮን /የ46 በመቶ/ ዕድገት አሣይቷል፡፡

አዋሽ ባንክ ባሣለፍነው የሂሣብ ዓመት 100 አዳዲስ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ለአገልግሎት ማብቃት የቻለ ሲሆን፣ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አዳዲስ የተቀማጭ ሂሣብ ደንበኞችን በማፍራት ጠቅላላ የተቀማጭ ሂሣብ ደንበኞቹን ከ5 ሚሊዮን በላይ ማድረስ ችሏል፡፡ የቅርንጫፎች መስፋፋት ህብረተሰባችን በየአካባቢው የባንክ አገልግሎቶችን እንዲያገኝ ከማስቻሉም በተጨማሪ አዳዲስ ደንበኞች የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያሳድጉ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ አዋሽ ባንክ ህብረተሰቡ በቦታና በጊዜ ሳይገደብ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የኤቲኤም፣ የሞባይል እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ባደረገው ጥረት እ.ኤ.አ. ሰኔ 2021 መጨረሻ ላይ 4 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አድርጓል፡፡ ይህም መንግስት የፋይናንስ አካታችነትን እና ተደራሽነትን ለማስፋፋት የሚያደርገውን ብርቱ ጥረት አጋዥ እንደሆነ ይታመናል፡፡

አዋሽ ባንክ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሰጠው ብድር መጠን በ2020/21 የሂሣብ ዓመት መጨረሻ ላይ የብር 30 ቢሊዮን /የ53 በመቶ/ ዕድገት በማሣየት ብር 87.1 ቢሊዮን ሆኗል፡፡

በውጭ ምንዛሪ ረገድም በ2020/21 የሂሣብ ዓመት ከተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ምንጮች ከ906 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ማግኘት የቻለ ሲሆን ይህም አሀዝ ከአምናው ተመሣሣይ ጊዜ አንጻር የ37 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ለዚህም ዋና ዋና ምክንያቶች የአለም ኢኮኖሚ ከኮቪድ ተጽእኖ ማገገም፣ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማደግ እና አዋሽ ባንክ የወሰዳቸው የተለያዩ የፖሊሲ እርምጃዎች ናቸው፡፡

አዋሽ ባንክ ከዛሬ 5 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የግል ባንኮች ታሪክ ከብር 1 ቢሊዮን በላይ ያልተጣራ ትርፍ አስመዝግቦ ታሪክ እንደሰራው ሁሉ ባሣለፍነው በጀት ዓመትም ከብር 5.58 ቢሊዮን በላይ ያልተጣራ ትርፍ በማስመዝገብ ሌላ ታሪክ ሰርቷል፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት የባንኩ ገቢ አምና ከነበረበት ከብር 10.2 ቢሊÄን ወደ ብር 13.7 ቢሊዮን ማደጉ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

አዋሽ ባንክ በተቀማጭ ሂሣብ፣ በብድር እና በትርፋማነት ብቻ ሣይሆን በተከፈለ ካፒታል መጠኑም የመሪነት ሥፍራውን እንደያዘ ቀጥሏል፡፡ የአዋሽ ባንክ የተከፈለ ካፒታል በዓመቱ በብር 2.23 ቢሊዮን ያደገ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ሰኔ 2021 መጨረሻ ላይ ብር 8.2 ቢሊዮን ደርሷል፡፡ ይህ መጠን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሁሉም ነባር የግል ባንኮች ለወደፊቱ በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ እንዲደርሱበት ካስቀመጠው የ5 ቢሊዮን ብር መጠን በእጅጉ የላቀ ነው፡፡ አዋሽ ባንክ በአሁኑ ጊዜ በ566 ቅርንጫፎች እና ከ12 ሺህ በላይ በሆኑ ሰራተኞች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

በየዓመቱ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የሚታወቀው አዋሽ ባንክ እ.ኤ.አ. በ2020/21 የሂሣብ ዓመት በተለያዩ የማህበረሰብ ልማት ስራዎች እና በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ለተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከብር 30 ሚሊዮን በላይ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

 

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Apr 18, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.8022 57.9382
GBP
67.5744 68.9259
EUR
60.4375 61.6463
AED
13.9956 14.2755
SAR
13.7039 13.9780
CHF
59.5391 60.7299

Exchange Rate
Close