አዋሽ ባንክ እና የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

አዋሽ ባንክ በሃገራችን እየተስፋፋ የመጣውንና በተለይ ባንኮችን ተጋላጭ የሚያደርገውን በውክልና ሰነዶች የማጭበርበር ወንጀል ለመከላከል የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ከፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር ነሃሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ተፈራርሟል። የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት የአዋሽ ባንክ ሆል ሴል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ታደሰ ገመዳ እና የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ናቸው፡፡
ስምምነቱ በተለይም የዉክልና ሰነዶችን ትክክለኛነትና ህጋዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀሎችን ለማስቀረት የሚያስችል መሆኑን የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረና የአዋሽ ባንክ ሆል ሴል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ታደሰ ገመዳ ገልፀዋል። ስምምነቱ ቀደም ሲል በዉክልና የሚንቀሳቀሱ የባንክ ሂሳቦችንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የዉክልናዉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በባንክ ባለሙያዎች ወደ ኤጀንሲዉ ይደወል የነበረዉን በማስቀረት ኦንላይን ለማረጋገጥ ስለሚያስችል ቀደም ሲል የነበረዉን እንግልትና የተንዛዛ አሰራር ሙሉ በመሉ የሚያስቀር ነዉ ተብሏል።

 

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Nov 28, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
55.6854 56.7991
GBP
67.1870 68.5307
EUR
60.9588 62.1780
AED
13.7216 13.9960
SAR
13.4363 13.7050
CHF
60.3764 61.5839

Exchange Rate
Close