አዋሽ ባንክ ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በባልቻ ሳፎ አዳራሽ ባካሄደው የ8ኛው ዙር “ከአዋሽ ይቀበሉ ይሸለሙ” የሎተሪ መርሐ ግብር አሸናፊ ለሆኑ እድለኞች ያዘጋጀዉን ሽልማት ሰጠ፡፡

አዋሽ ባንክ  ከ ታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም አስከ ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ተከታታይ ወራት ሲያካሂድ የነበረውን የ8ተኛ ዙር ከአዋሽ ይቀበሉ ይሸለሙ  የሎተሪ ፕሮግራም አጠናቆ አሸናፊ ለሆኑት ዕድለኞች ያዘጋጀዉን ሽልማት ሰጠ፡፡

ባንካችን ከአዋሽ ይቀበሉ፤ያሸንፉ የሎተሪ ዕጣ መርሀ ግብር ሲያዘጋጅ ሶስት ዋና ዋና ዓላማዎችን ታሳቢ በማድረግ ነበር፡፡

የመጀመሪያው ለአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት በጣም አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ ፍሰት እንዲጨምር ማድረግ ነው፡፡

ሁለተኛው ዓላማ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ አገራችን የሚመጣው የውጭ ምንዛሪ በሕጋዊ መንገድ እንዲመጣ ለማድረግና የሚገኘውም የውጭ ምንዛሪ ለአገራችን ልማትና ዕድገት እንዲውል ለማስቻል ነው፡፡

ሦስተኛው ዓላማችን ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተላከላቸውን የውጭ አገር ገንዘቦች በአዋሽ ባንክ በኩል የሚቀበሉ ወይም አምጥተው ሚመነዝሩ ደንበኞቻችን በሽልማት መልክ ማበረታቻ እንዲያገኙ ነው፡፡

ከዚህ አኳያ ላለፉት ስምንት ተከታታይ ዙሮች ያደረግነው የሎተሪ ማበረታቻ ሥነ-ሥርዓት በአብዣኛው የተቀመጠላቸውን ግቦች ማሳካት ችለዋል፡፡ በእሰካሁኑ የባንካችን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማበረታቻ የሎተሪ መርሐ ግብር መኪና  የሚያስገኘውን ዕጣ ያሸነፉት  በመምህርነት፣ በልብስ ስፌት፣ በግብርና፣ በፖሊስነት፣ በቀን ሰራተኝነትና  እና በትናንሽ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ናቸው፡፡

ባንካችን የአገራችንን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ “ከአዋሽ ይቀበሉ ያሸንፉ” መርሃ ግብር በተጨማሪ የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡  በተለይም ከውጭ ሀገራት በሃዋላ መልክ ወደ አገራችን የሚላከውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ በአሁኑ ጊዜ ከ17 በላይ ከሚሆኑ የሃዋላ ሰጪ ድርጅቶች ጋር እየሰራ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ “PayPal” ከተባለ ታዋቂ ዓለም ዓቀፍ የሃዋላ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ጋር በመሆን በብቸኝነት አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡

ባንካችን ተግባሩ  ልክ እንደ መሪ ቃሉ  የደንበኞቹን ፍላጎት ማርካት እንደመሆኑ መጠን የገባውን ቃል በማክበር ስምንተኛውን ዙር “ከአዋሽ ይቀበሉ ያሸንፉ” መርሐ ግብርን ከታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ግንቦት 19  ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ የስምንተኛው ዙር “ከአዋሽ ይቀበሉ ያሸንፉ” የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ የሎተሪ መርሐ ግብርም ልክ እንዳለፉት ሰባት ዙሮች  በተሳካ ሁኔታ  ተጠናቆ ዕጣው ሐምሌ 21 ቀን 2012 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ  በይፋ ወጥቷል፡፡

ለስምንተኛው ዙር መርሐ ግብር የተዘጋጁት የሽልማት ዓይነቶች በሶስት ደረጃዎች የተከፋፈሉ ሲሆኑ ለአንደኛው ዕጣ የተዘጋጀው የሽልማት ዓይነት ብር 1,650,000. 00 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ) የሚያወጣ አንድ አይሱዙ ዘመናዊ የጭነት መኪና ፣ ለሁለተኛ ዕጣ (አራት ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው 32 ኢንች ኤልኢዲ ቴሌቪዥኖች እና ለሶስተኛ ዕጣ (አምስት ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው ዘመናዊ የውሃ ማጣሪያ እና አራተኛ ዕጣ (ሃያ ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው ስማርት የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ናቸው፡፡

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባወጣው ዕጣ መሰረትም ብር 1,650,000.00 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ) የሚያወጣ አይሱዙ ዘመናዊ የጭነት መኪና የሎተሪ ቁጥር 055781 የያዙት አቶ አብደላ ቃሲም አብዩ ከዶዶላ ከተማ  ዶዶላ ቅርንጫፋችን የተላከላቸውን የውጭ ምንዛሪ ተቀብለው አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሌሎች በርካታ ለሎተሪ ዕጣው የተዘጋጁ ሽልማቶችም ለዕድለኞች ደርሰዋል፡፡

 

 

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Dec 02, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
123.8587 126.3358
GBP
152.2681 155.3135
EUR
134.2996 136.9856
AED
30.5175 31.1278
SAR
29.8784 30.4759
CHF
134.6594 137.3526

Exchange Rate
Close