አዋሽ ባንክ ተግባራዊ ያደረገዉ አዋሽ ኢ-ስኩል ማኔጅመንት ሲስተም ከባንኩ ጋር ለሚሰሩ ት/ቤቶች፣ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲወች የት/ት ክፍያ አሰባሰብ እና የት/ቤት አስተዳደር ስራቸዉን ለማዘመን በነጻ እንዲገለገሉበት የተበረከተ ነዉ።

ይህ እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጅ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ ወላጆች እና ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን የሚሰጣቸዉን የይለፍ ቃል በመጠቀም በቀጥታ ወደ Awash E-School Management System በመግባት የሚከተሉት ዋና ዋና አገልግሎቶች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፣

  1. ለመምህራን
  • School Planner (የትምህርት ማቀጃ)፣
  • Subject and Assessments (ትምህርት እና ምዘና)፣
  • E-Learning (የገጽ ለ ገጽ ትምህርት የሚሰጡበት)፣ እና
  • E-library (ኤሌክትሮኒክስ ቤተ መጻህፍት አገልግሎት የሚያገኙበት እና ለተማሪዎች የሚያጋሩበት)፣
  1. ለአስተዳደር ሰራተኞች
  • Finance and Payment፡ የት/ት ክፍያቸዉን በተቀላጠፈ እና ለወላጆች ምቹና ተደራሽ በሆኑ ሶስት አማራጮች (በአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎችበአዋሸብር ወኪሎች እና በአዋሽብር ሞባይል ባንኪንግ) መሰብሰብ ያስችላቸዋል፡፡
  • Penalty Management (የቅጣት ክፍያ መቆጣጠሪያ)፣
  • Reconciliation (የሂሳብ ማስታረቂያ)፣
  • Student Information (የተማሪዎች መረጃ የሚያደራጁበት)፣
  • Staff Information (የሰራተኞች መረጃ የሚያደራጁበት)፣
  • Notice Board (ዲጂታል ማስታወቂያ ሰሌዳ)፣
  • Bulk Message (አጭር መልእክት ለበርካታ ወላጆች በአንድ ጊዜ መላክ የሚያስችል)፣
  • Report Center (ዝርዝር ሪፖርት ማውጫ)
  1. ለወላጆች እና ተማሪዎች
  • የት/ት ክፍያቸዉን በአቅራቢያቸዉ በሚገኙ የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎችየአዋሸብር ወኪሎች እንዲሁም በአዋሽብር ሞባይል ባንኪንግ በማንኛዉም ጊዜ አና ባሉበት ቦታ ሆነዉ በመክፈል ጊዚያቸዉን መቆጠብ እና ምቾታቸዉን መጠበቅ ያስችላቸዋል፡፡
  • ከት/ቤታቸዉ የሚላክላቸውን መልዕክቶች ማየት፣
  • የተሰጡ የቤት ሰራዎችን ባሉበት ቦታ ሆነው የተሰጣቸዉን የቤት ስራ ሰርተው ማስገባት፣
  • የፈተና የጊዜ ሰሌዳዎችን የሚያዩበት፣
  • ዲጅታል መጽሀፍቶችን የሚያገኙበት፣
  • የፈተና ዉጤታቸዉን የሚያዩበት፣ እና
  • በ Online የሚሰጡ ትምህርቶችን መከታተል የሚያስችላቸው ዘመናዊ ቴክኖሎጅ ነው።

የአዋሽ ኢ-ስኩል ማኔጅመንት ሲስተምን ለመጠቀም ት/ቤቶች፣ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች አቅራቢያቸዉ የሚገኙ የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎችን ማናገር ወይም በ8980 በመደወል ከባንካችን የጥሪ ማእከል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Mar 12, 2026 - EXCHANGE Rate
CurrencyCash and Remittances through AgentsTransaction
BuyingSellingBuyingSelling