አዋሽ ባንክ በከባድ ዝናብ ቤታቸው ለወደመባቸው አርሶ አደሮች የቆርቆሮ ድጋፍ አደረገ።

ለማህበረሰብ መቆርቆርን አንኳር እሴቱ ያደረገው አዋሽ ባንክ በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ በከባድ ዝናብ ቤታቸው ለወደመባቸው አርሶ አደሮች የቆርቆሮ ድጋፍ አድርጓል።
በሰሜን ሜጫ ወረዳ ሰኔ 4 እና ሰኔ 9/2014 ዓ.ም በጣለው በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በ9 ቀበሌ 2ሺህ 631 አርሶ አደሮች የመኖሪያ ቤት፣ አትክልትና ፍራፍሬ ሌሎች ሰብሎችም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የተናገሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንተነህ ወንዱ፣ አዋሽ ባንክ 1ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በሚሆን ወጪ ለተጎጂ አርሶ አደሮች ድጋፍ በማድረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
አዋሽ ባንክ ከምስረታው ጀምሮ የፋይናንስ አገልግሎቱን ተደራሽ ከማድረጉም ባሻገር በማንኛውም ወቅት ድንገተኛ አደጋዎች በሚያጋጥሙ ጊዜም ከማህበረሰቡ ጎን መቆሙን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዋሽ ባንክ ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሠረት አምበሉ በድጋፍ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ገልፀዋል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Sep 29, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
55.2224 56.3268
GBP
64.2394 65.5242
EUR
58.5247 59.6952
AED
13.6041 13.8762
SAR
13.3217 13.5881
CHF
57.7817 58.9373

Exchange Rate
Close