አዋሽ ባንክ “በአዋሽ ይቆጥቡ ይቀበሉ ይሸለሙ” አሸናፊ ለሆኑ እድለኞች ያዘጋጀዉን ሽልማት አስረከበ

አዋሽ ባንክ ከግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም አስከ ጥር 11 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ሲያካሂድ የነበረውን የ9ኛው ዙር “በአዋሽ ይቆጥቡ ይቀበሉ ይሸለሙ” የሎተሪ መርሐ ግብር አሸናፊ ለሆኑ እድለኞች ያዘጋጀዉን ሽልማት አስረከበ፡፡
ለዘጠነኛው ዙር መርሐ ግብር የተዘጋጁት የሽልማት ዓይነቶች በአምስት ደረጃዎች የተከፋፈሉ ሲሆን ለአንደኛው ዕጣ የተዘጋጀው የሽልማት ዓይነት አንድ አይሱዙ ዘመናዊ የጭነት መኪና የሎተሪ ቁጥር 00027805864 የያዙት አቶ ሀብታሙ ወልዴ ፋንታሁን በጅማ ከተማ ጅሬን ቅርንጫፍ የባንክ አገልግሎት ባገኙበት ወቅት በተሰጣቸው የሎተሪ ዕጣ ቁጥር አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ለ2ኛ እጣ የተዘጋጀው ኪያ ፒካንቶ የቤት አውቶሞቢል የሎተሪ ቁጥር 00027414628 የያዙት አቶ በላቸው ስሜ አዱኛ ከገርባ ጉራቻ ከተማ ከገርባ ጉራቻ ቅርንጫፍ የደረሳቸው ሲሆን ለሶስተኛ ዕጣ (አስር ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው ዘመናዊ ላፕቶፖች፣ ለአራተኛ ዕጣ (ሰላሳ ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው 32 ኢንች ኤልኢዲ ቴሌቪዥኖች እንዲሁም ለአምስተኛ እጣ (ሀምሳ ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው ስማርት የሞባይል ስልክ ቀፎዎችን ዕጣ ለወጣላቸው ለዕድለኞች ሽልማታቸውን አስረክቧል፡፡
በሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ለሎተሪ ዕጣ አሸናፊዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ እንደገለፁት ባንኩ ያዘጋጀው የሎተሪ መርሐ ግብር የማህበረሰቡን የቁጠባ ባህል በማሳደግ የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ግንዛቤን ከመፍጠሩም ባሻገር ለአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ ፍሰት በሕጋዊ መንገድ እንዲመጣ በማድረግ የሚገኘውም የውጭ ምንዛሪ ለአገራችን ልማትና ዕድገት እንዲውል ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ረገድ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ለመርሐ ግብሩ መሳካት ያልተቆጠበ ድጋፍ ላደረጉት የመንግስት፣ የግል ድርጅቶችና ግለሰቦችን ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Jul 26, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
57.4895 58.6393
GBP
70.6759 72.0894
EUR
62.3359 63.5826
AED
14.1646 14.4479
SAR
13.8682 14.1456
CHF
62.5028 63.7529

Exchange Rate
Close