አዋሽ ባንክ በባሌ ሮቤ ባለ 4 ወለል ህንፃ ሊገነባ ነው

በአገራችን የግል ባንኮች ታሪክ የራሱን ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ በመዲናችን በማስገንባት ቀዳሚ የሆነውና  በዋና ዋና የክልል ከተሞችም የራሱን ህንፃዎች በማስገንባት የሚታወቀው አዋሽ ባንክ በኦሮሚያ ብሔራዊ  ክልላዊ  መንግስት ባባሌ ዞን ዋና ከተማ ሮቤ ባለ አራት ወለል ህንፃ ሊገነባ ነው፡፡

የህንፃውን አርክቴክቸራል ዲዛይን ከሰሩት ተወዳዳሪዎች አሸናፊዎችን ለመምረጥ  በተዘጋጀው መድረክ ላይ  የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዋሽ ባንክ  ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው  እንደገለጹት  ባንኩ በአዲስ አበባ ከተማ ከዋናው መስሪያ ቤት በተጨማሪ ባለ አስር ወለልና ሁለት ምድር ቤት ያለው ህንፃ ከማሰገንባቱም ውጪ  ከአዲስ አበባ ውጪም ባለፉት ዓመታት  የራሱን ህንፃዎች ለመገንባትም ሆነ የተገነቡትን ለመግዛት ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ የተገነቡትና የተገዙት ህንፃዎች በአዳማ፣በሐዋሳ፣በሻሸመኔ፣በነቀምቴ፣በጊምቢ፣በአጋሮ፣በሃረር፣በቢሾፍቱ እና በበዴሳ የሚገኙ ሲሆን ህንፃዎቹ የባንካችን ደንበኞች የተመቻቸ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማስቻላቸውም በላይ ለባንኩ ሠራተኞችም ምቹ የሥራ አካባቢን ፈጥሯል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው፣  ለየቅራንጫፎቹ ይወጣ የነበረውን የቢሮ ኪራይ ወጪን በመቀነስ ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽአ ማበርከቱን አስረድተዋል፡፡

ባንካችን በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ከተሞች በየዓመቱ የቅርንጫፍቹን ቁጥር ለማስፋትና ተደራሽነቱን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል ያሉት አቶ ፀሐይ  የባሌ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው በሮቤ ከተማ ሕንፃ ለመገንባት የተፈለገበት ዋናው ምክንያትም ከተማዋ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ ከተሞች አንዷ ከመሆኗም በላይ የባንኩ ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚካሄድባቸው  ከተሞች መካከል ሮቤ አንዷ በመሆኗ ነውም ብለዋል፡፡ የሚሠራው ሕንፃ ጠቅላላ ቦታ ስፋት 1560 ሜትር ካሬ ሲሆን ቦታው በከተማው ውስጥ ለንግድና ለተለያዩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ተፈላጊ ሥፍራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የህንፃውን አርክቴክቸራል ዲዛይን በእውቅ ድርጅቶች ለማሰራት በመገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያ እንዲነገር በመደረጉ 29 ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን የገዙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 14ቱ ስራውን ለመስራት ብቁ የሚያደርጋቸውን መስፈርት አሟልተው እንዲወዳደሩ ተደርጓል፡፡ ውድድሩም ፍትሐዊነት እንዲኖረውና ጥራት ያለው ስራ እንዲሰራ በማሰብ ከኢትዮጵያ አርክቴክቸራል  ዲዛይን ማህበር ሙያዊ ትብብር በመጠየቅ የመወዳደርያ መስፈርቶችን በማዘጋጀት ውድድሩን እንዲዳኙ ሶስት አባላትን ያካተተ ገለልተኛ ኮሚቴ ተቋቁሞ አሸናፊ ድርጅትን የመለየት ስራ መከናወኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው አስረድተዋል፡፡ በተዘጋጀው የመወዳደርያ መስፈርትም MTT አርክቴክትና ኢንጂነሪንግ አማካሪ ድርጅት መመረጡን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Nov 28, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
55.6854 56.7991
GBP
67.1870 68.5307
EUR
60.9588 62.1780
AED
13.7216 13.9960
SAR
13.4363 13.7050
CHF
60.3764 61.5839

Exchange Rate
Close