አዋሽ ባንክ ለጎዳና ተዳዳሪዎች እና ለአቅመ ደካሞች የምገባ መርሐ-ግብር የሚውል የብር 200,000 ሺህ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ::

ባንኩ የ4ኛውን ዙር የምገባ ፕሮግራም ከኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፣ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዲሁም ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም ነሀሴ 2 ቀን 2012 ዓ.ም አስጀምረውታል ።

የምገባ ፕሮግራሙ ቀደም ሲል ሲካሄድ የቆየው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በጋራ ለማሸነፍ የኢፊድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የማዕድ ማጋራት ብሔራዊ ጥሪ ተከትሎ ሲሆን አዋሽ ባንክን ጨምሮ የተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች እና ባለሃብቶች ባደረጉት ድጋፍ የምገባ ፕሮግራሙ ለ4ኛ ወር ሊቀጥል ችሏል ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዱቤ ጅሎ እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ጀምሮ ኮሚሽኑ የተለያዩ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን እየተወጣ መሆኑን ጠቁመው ፤ይህ የምገባ ፕሮግራምም በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ አዋሽ ባንክ ላደረገው ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ም/ኮሚሽነሩ አያይዘውም እስካሁን በተደረገው የምገባ ሂደት እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች የዕለት ምግብ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር ለወረርሽኙ ያላቸው ተጋላጭነት እንዲቀንስ እንዲሁም የተወሰኑት ቋሚ ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተ/ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር “ለወገን ደራሽ ወገን ነው’’ የሚለውን ብሂል በመከተል ወጋችንን እና ባህላችንን ጠብቀን የተለያዩ አካላትን ድጋፍ በመጠየቅ የምገባ ፕሮግራሙ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንሰራለን ብለዋል ፡፡

አዋሽ ባንክ ከምስረታው ጀምሮ የፋይናንስ አገልግሎቱን ተደራሽ ከማድረጉም ባሻገር የማህበረሰቡን ችግር በመረዳት እገዛና ድጋፍ በማድረግ ላይ ሲሆን በተለይ የኮሮና ቫይረስ በሃገራችን ከተከሰተ ግዜ ጀምሮ ማህበራዊ ሃላፊነቱን በሚገባ በመወጣት ላይ እንደሚገኝና በቀጣይም በሚደረጉ በጎ ተግባሮች ላይ ከመንግስት ጎን በመቆም ጉልህ ድርሻ እንደሚጫወት ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

May 29, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
57.0384 58.1792
GBP
69.4569 70.8460
EUR
61.9494 63.1884
AED
14.0523 14.3333
SAR
13.7631 14.0384
CHF
59.6100 60.8022

Exchange Rate
Close