አዋሽ ባንክ ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የትምህርት ቁሳቁሶችን አበረከተ..

አዋሽ ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አነሳሽነት በተጀመረው ‘ስጦታ ለአዲስ አበባዬ’ የበጎ አድራጎት ንቅናቄ መሰረት በመስተዳድሩ በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን  በመንግስት ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን  ለሚከታተሉ ተማሪዎች የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ማህበራዊ ሃላፊነት ለመወጣት በማሰብ 659,584 የመማሪያ ደብተሮችን ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ አውጥቶ በመግዛት ነሐሴ 10 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት በመገኘት ለከተማ መስተዳድሩ አበርክቷል፡፡ ባንኩን በመወከል ስጦታውን ያበረከቱት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታቦር ዋሚ እና  የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ዮሐንስ መርጋ ሲሆኑ ከተማ አስተዳደሩን በመወከል ስጦታውን የተረከቡት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ናቸው፡፡

ምክትል ከንቲባው ስጦታውን በተረከቡበት ወቅት አዋሽ ባንክ ቀደም ሲልም በተለያዩ ዘርፎች ላይ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ መቆቱን በማውሳት  ባንኩ ለሃገር ተረካቢ ተማሪዎች ላደረገው ተምሳሌታዊ የሆነ ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ሌሎች ተቋማትም መሰል ድጋፎችን በማድረግ ለዚህ የተቀደሰ ዓለማ ላለው ታሪካዊ ጥሪ በጎ ምላሽ በመስጠት ከከተማ መስተዳድሩ ጎን እንዲቆሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ አዋሽ ባንክን በመወከል ስጦታውን ለክቡር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ያስረከቡት የባንኩ የዳይሬክሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታቦር ዋሚ በበኩላቸው አዋሽ ባንክ ለትርፍ የተቋቋመ ተቋም ቢሆንም ተቀዳሚ ተልዕኮው ግን ለማህብረሰቡ በተለይም ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ በግንባር ቀደምነት በመገኘት የበኩሉን ጉልህ አሻራ ማሳረፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህ ‘ስጦታ ለአዲስ አበባዬ’ በተሰኘው መልካም አላማን አንግቦ ለተነሳው ግብ መሳካት ባንኩ የበኩሉን ለመወጣት ካለው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ የተበረከተው ደብተር በገንዘብ ሲተመን ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የገለፁት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ፣  አዋሽ ባንክ በኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት ፕሮግራሙ በየዓመቱ ከፍተኛ በጀት በመመደብ በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ ላሉት ማህበራዊ ግላጋሎት ሰጪ ለሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

በሌላም በኩል አዋሽ ባንክ የማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለተፈናቀሉ እና በድንገተኛ አደጋ ለተጐዱ እንዲሁም በፌደራል እና በክልል መንግሥት ደረጃ ለታቀዱ የዕድገት እና የልማት ኘሮጀክቶች በከፍተኛ ደረጃ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀው በቅርቡ በክቡር ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት ለተጀመረው የሸገር ማስዋብ ፕሮግራምም ባንኩ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን በማውሳት ይህንን መሰል ተግባር ለወደፊቱም አጠናክሮ በመቀጠል ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በሁሉም መስክ እንደሚያረጋግጥም  አስታውቀዋል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Jun 07, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
54.3747 55.4622
GBP
64.4580 65.7472
EUR
58.1483 59.3113
AED
13.3964 13.6643
SAR
13.1217 13.3841
CHF
57.2144 58.3587

Exchange Rate
Close