አዋሽ ባንክ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ 25 ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዢ አከናወነ !

በአገራችን ኢኮኖሚ ውስጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ያለውና ኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነቱን በተለያዩ ዘርፎች እየተወጣ ያለው ባንካችን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቦንድ በመግዛትና ገንዘብ በመለገስ አስፈላጊውን የፋይናንስ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ የአገራችንን ታሪክ ከመሰረቱ እየቀየረ ባለው ታላቅ ፕሮጀክት ላይም ባንካችን የራሱን አሻራ እያኖረ በመሆኑም ደስታችን ወደር የለውም፡፡

ስለሆነም ልክ እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ ዛሬም ታላቁ የአገራችን ህዳሴ እና ህልውና መሰረት የሆነው ግዳባችን አሁን ባለበት ደረጃ ላይ በመድረሱ ታላቅ ደስታ እንደተሰማን እየገለጽን ቀሪው ስራ በተያዘለት ዕቅድ መሰረት ተጠናቆ ለአገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የድርሻውን እንዲያበረክት፣ ህዝባችንም በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አግኝቶ ኑሮውን እንዲያዘምን በባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድና የስራ አመራር ውሳኔ መሰረት የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ በብር 25 ሚሊዮን የቦንድ ግዢ አከናውነናል፡፡ በዚህም የአገራችን የልማት አጋር በመሆናችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል፡፡

 

 

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Jun 08, 2023 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
54.3861 55.4738
GBP
64.6741 65.9676
EUR
58.2693 59.4347

Exchange Rate
Close