የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች ህዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄዱት 16ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቀደም ሲል በ14ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉበኤ ላይ የባንኩ ካፒታል ከብር 3 ቢሊዮን ወደ ብር 6 ቢሊየን እንዲያድግ የተወሰነው የክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ ተሻሽሎ እ.ኤ.አ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2020 እንዲሆን የወሰኑ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የተደለደለላችሁን አክሲዮን ፈርማችሁ ክፍያዎቻችሁን ያላጠናቀቃችሁ የባንኩ ባለአክሲዮኖች እ.ኤ.አ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2020 ድረስ የሚጠበቅባችሁን ክፍያ በሕጉ መሠረት እንድትፈፅሙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልተከፈለ በሕጉ መሰረት ተጨማሪ አክሲዮኖች ለመግዛት ተመዝግበው እየተጠባበቁ ለሚገኙ ሌሎች ባለአክሲዮኖች የሚተላለፍ መሆኑን በትህትና ይገልፃል፡፡
የአዋሽ ባንክ
ዳይሬክተሮች ቦርድ