የአዋሽ ባንክን ብራንድ ጠብቆ ባንኩን እና ደንበኞቹን በሚመጥን መልኩ የታደሰው እና በአዋሽ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ስር የሚገኘው ፊንፊኔ ልዩ ቅርንጫፍ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ ከፍተኛ የስራ አመራር እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቆ ስራ ጀመሯል። የተደረገው እድሳትም ለባንኩ ድንበኞች እና ሠራተኞች ምቹ የስራ አካባቢን እና የላቀ የደንበኞች አገልግሎት እንዲሁም ተሞክሮ ማሻሻልን ታሳቢ አድርጎ የተሰራ ነው።