አዋሽ ባንክ ‘’ባንክዎ በእጅዎ’’ በሚል መሪ ቃል ከህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የዲጂታል ባንኪንግ ንቅናቄ ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በደማቅ ሁኔታ አካሄደ፡፡
በዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓቱ ላይ የባንኩ ሲኒየር ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር አቶ ዮሃንስ መርጋ እንደገለጹት የዲጂታል ባንኪንግ ንቅናቄ ዋና አላማ ሶስት ቁልፍ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን ማለትም አዋሽ ብር ፕሮ ሞባይል ባንኪንግ፣ መርቻንት እና የፖስ አገልግሎቶችን ኢላማ ያደረገ መሆኑን አመላክተው ከባንኩ ጋር አብረው እየሰሩ ለሚገኙ ክቡራን ደንበኞች እና ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡