ለበርካታ አመታት የማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንፃር ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ የሚገኘው አዋሽ ባንክ በሠራተኛና ክህሎት ሚኒስቴር ሥር ከሚገኘው የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) ጋር በመተባበር በባህር ዳር ፣ በመቀሌ እና በሰመራ ከተማ ከሚገኙና ከተለያዩ ማዕከላት ለተውጣጡ ቁጥራቸው 145 ለሚሆኑ ለጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የአቅም ግንባታ የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና የሰጠ ሲሆን መርሐ ግብሩ በሃገር አቀፍ ደረጃ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ባንኩ በቀጣይም ዘርፉን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡