የ6ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ሥነ-ሥርዓት በትናንትናው እለት በብሔራዊ ቤተ-መንግስት በተካሄደበት ወቅት ባንካችን ከፍተኛ ግብር በታማኝነት በመክፈሉ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእዉቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
በፋይናንስ ዘርፉ ፈር ቀዳጅ የሆነውና 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘው አዋሽ ባንክ የአገልግሎት አድማሱን ከማስፋቱም ባሻገር የወገኖቻችንን ህይወት ለማሻሻል የሚረዱ ተግባራትን በሃላፊነት መንፈስ በመወጣት ላይ ይገኛል። ባንካችን ይህን ማህበራዊ ግዴታውን የመወጣት ተግባር ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማረጋገጥ ይወዳል፡፡