አዋሽ ባንክ እ.አ.አ በ2023/24 ሂሳብ ዓመት 11.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገበ።

በ2023/24 የሂሳብ ዓመት የባንካችን ጠቅላላ ገቢ በ27 በመቶ እድገት በማሳየት ብር 36.4 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ባንካችን በዓመቱ ከ depreciation እና provision በፊት ብር 11.6 ቢሊዮን ለማትረፍ ችሏል።
በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ኤልሲ ማርጂንን ጨምሮ ብር 232 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ45.1 ቢሊዮን ብር ወይም በ24 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡
በተያያዘም ባንካችን እ.ኤ.አ በ2023/24 የሂሳብ ዓመት 1.5 ቢልዮን የአሜሪካን ዶላር በላያ የውጭ ምንዛሪ ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃር ሲታይ የ26.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፡፡
አዋሽ ባንክ በሂሳብ ዓመቱ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በድምሩ 137.6 ቢሊዮን ብር በላይ አዳዲስ ብድሮችን ሰጥቷል። በዚህም የባንኩ የብድር መጠን በአመቱ መጨረሻ ላይ ብር 183 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ልዩ ትኩረት በመስጠት ከብር 5.2 ቢሊዮን በላይ ብድር በጣም ጥቃቅን ለሆኑ ስራዎች (Business) ማመቻቸት የቻለ ሲሆን ባንኩም አነስተኛ እና ጥቃቅን ዘርፉን ለማበረታታት በያዘው አቅጣጫ መሰረት ለዘርፉ የተሰጠው ብድር እ.ኤ.አ በጁን 30፣ 2024 ብር 45.5 ቢሊዮን ደርሷል።

Dec 21, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
124.6101 127.1023
GBP
153.1919 156.2557
EUR
135.1144 137.8167
AED
30.7026 31.3167
SAR
30.0597 30.6609
CHF
135.4765 138.1860

Exchange Rate
Close