አዋሽ ባንክ በ2022/23 የመሪነት ስፍራውን በማስጠበቅ በሂሳብ ዓመቱ ከፍተኛ ትርፍ አስመዘገበ፡፡

(አዲስ አበባ ህዳር 15/2016 .) አዋሽ ባንክ የባለአክሲዮኖች 28ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 15 ቀን 2016ዓ.ም በእስካይላይት ሆቴል ተካሂዷል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት፣ ቀደም ሲል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከስከተለው ተጽኖና  የዓለም ኢኮኖሚ ሳያገግምና ሌሎች ተግዳሮቶች በኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ በቀጠለበት እና በአገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ነባራዊ ሁኔታ  በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ ተፅዕኖ በፈጠረበት ሁኔታ በሌላ በኩልም በስሜንና በምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች የሰላም እጦት በቀጠለበት ሁኔታ ውስጥም ሆኖ  አዋሽ ባንክ በአስር ዓመቱ ፍኖተ ካርታው ላይ ባስቀመጠው ስትራቴጂ በመመራትና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ቀውሶችን ለመቆጣጠር የሚያስችሉትን ስትራቴጂዎችን በመተግበር የበጀት ዓመቱን በአመርቂ ውጤት ማጠናቀቁን የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጉሬ ኩምሳ ዓመታዊ ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤው  ባቀረቡበት ወቅት ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩልም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄደው የዋጋ ንረት፣በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የነበሩ የፀጥታ ስጋቶች ፣በባንኮች መካከል ያለው ከፍተኛ ፉክክር እያደገ የመጣበት ዓመት የነበረ ቢሆንም ባንካችን ያስመዘገበው አኩሪ ውጤት ከቀደሙት ዓመታት እጅጉን የላቀና ባንኩ በየጊዜው የሚያስመዘግባቸው ተከታታይ ዕድገቶች ባንኩን በጠንካራና አስተማማኝ መሠረት ላይ እንዳቆመው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው በሪፖርታቸው ጠቁመዋል፡፡

ይህ አመርቂ ውጤት ሊገኝ የቻለው የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድና የስራ አመራር አባላት ተቀናጅቶ መስራትና በየደረጃው ያሉ የባንኩ ሠራተኞች ባሳዩት ከፍተኛ የስራ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ነው ያሉት አቶ ጉሬ ኩምሳ የበኩላቸውን አስተወፅኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በበኩላቸው 2022/23 የሂሳብ ዓመት አዋሽ ባንክ እንደወትሮ ሁሉ መንግስት በአገሪቱ የተስተዋሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች  የሚያስከትሉትን ጉዳቶች ለመቀነስ ለሚያደርገው ጥረት ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ህዝባዊነቱን ያስመሰከረበት ዓመት ከመሆኑም ባሻገር ባስመዘገበው ዓመታዊ ትርፍም ከግል ባንኮች መሪነቱን ጨብጦ መዝለቅ ችሏል ብሏል፡፡

ባንኩ በዘርፉ የሚታየውን ከፍተኛ ፉክክር እና ሌሎች ጫናዎችን በመቋቋም ባለፈው በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፍ እጅግ በጣም አመርቂ የሚባል ውጤት ከማስመዝገቡም ባሻገር ግሎባል ፋይናንስ የተሰኘው ዓለም ዓቀፍ ተቋም ከኢትዮጵያ በብቸኝነት በመመረጡ ለባንኩ የተዘጋጀውን ሽልማት ሞሮኮ ማራካሽ ከተማ በተካሄደው ስነስርዓት ላይ ባንኩ   ሽልማቱን መቀበሉንና እንዲሁም ባንኩ ለጥቃቅንና አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ዘርፎች ለሰጠው ትኩረት እቅውና በመስጠት ግሎባል ኤስምኢ ፋየይናንስ እውቅና ያገኘ ሲሆን የእውቅና ሽልማቱንም ባንኩ በህንድ ሙምባይ በመገኘት መቀበሉን ገልጸዋል ፡፡

 አዋሽ ባንክ በ2022/23 የሒሳብ ዓመት ማጠናቀቂያ ላይ ከመሰረታዊ የፋይናንስ አፈፃፀሞች አንፃር በተቀማጭ ገንዘብ እኤአ ከ2021/22 ጋር ሲነጻጸር የ23 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ወይም የብር 35.4 ቢሊዮን በመጨመር የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ሂሳብ ብር 187.4 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ይህም በባንኩና በግል ባንኮች ታረክ ውስጥ ከፍተኛ መሆኑ ታውቋል፣ በውጭ ምንዛሪ ግኝት ረገድም በሂሳብ  አመቱ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ 1 ቢሊዮን አራት መቶ ዘጠና ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር  ሲሆን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሁለት መቶ ሀምሳ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዕድገት አሳይቷል፡፡በብድር  ረገድ  በሂሳብ አመቱ ውስጥ የብር 40.9 ቢሊዮን ለተለያ ክፍላተ ኢኮኖሚዎች የተሰጠ ሲሆን የ22.3 በመቶ ዕድገት ባመስመዝገብ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሰጠው የብድር መጠን ብር 224 ቢሊዮን ለማድረስ ተችሏል፡፡ በሌላ መልኩ በበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠን ብር 224 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ደግሞ እ.ኤ.ኤ.  ሰኔ 30 ቀን 2022 ከነበረበት ብር 10.2 ቢሊዮን የብር 4.4 ቢሊዮን ወይም የ42 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ እ.ኤ.አ ሰኔ 30 ቀን 2023 መጨረሻ ላይ ብር 14.6 ቢሊዮን ደርሷል፡፡ ይህም ብሔራዊ ባንክ ነባር ባንኮች በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊደርሱበት ይገባል ብሎ ካስቀመጠው የካፒታል መጠን እጅጉን የሚበልጥ ነው፡፡   እ.ኤ.አ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2027 የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ብር 43 ቢሊዮን ለማድረስም ተወስኗል፡፡ ባንኩ በበጀት ዓመቱ ያስመዘገበው የትርፍ መጠን ብር 9.8 ቢሊዮን ሲሆን ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የብር 2.3 ቢሊዮን ወይም የ31 ከመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተመልክቷል፡፡ይህም በግል ባንኮች ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጷል፡፡

አዋሽ ባንክ የአገሪቱን ልማት ከመደገፍ አንፃር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት ባሻገር በተለያዩ ጊዜያት በመንግስት ለሚደረጉ አገራዊ ጥሪዎች ምላሽ መስጠቱ እንዳለ ሆኖ በስራ ፈጠራ ላይ የተሰማሩትን ለማበረታት ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ በአማርኛ ታታሪዎቹ በአፋን ኦሮሞ ቀጠሌዋን የተሰኘውን ፕሮጀክት በመንድፍ በተደረገው ውድድር ለአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት ያደረገ ሲሆን በሁለቱም ቋንቋዎች አንደኛ ለወጡ ያለምንም የብደር መያዧ የንብረት ዋስት ለያንዳንዳቸው የብር 5 ሚሊዮን ብድር ሰጥቷል፡፡ እንዲሁም ለተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶችም በሚሊዮን የመቆጠር  የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የባንኩን ሀብት ለማሳደግ፣ ለቅርንጫፎች ኪራይ የሚያወጣውን ወጪ ለመቀነስና በተለያዩ ከተሞች ህንፃዎችን በመገንባት ለከተሞች ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ ከማርከት አንፃርም ባንኩ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ከዚህ አንፃር በአዲስ አበባ የቡልቡላ ህንፃ ግንባታው በህንጻው ተቋራጭ ችግር ምክንት ግንባታው የቀመ ቢሆንም ግንባታውን ለማጠናቀቅ ዝግጅት እየተደረገሲሆን የባሌ ሮቤ ህንጻ ግንባታ ተጠናቆ ህዳር 6 ቀን 2016 አ.ም ተመሪቋል፡፡ በአሰላ ከተማ እየተገነባ ያለው የባንኩ ህንጻ ግንባታው በመፋጠን ላይ ነው፡፡  በድሬደዋ ከተማ አዲስ ለሚገነባ ህንፃ የአርክቴክቼራል ዲዛይን ስራ የተሰራ ሲሆን በሌላ በኩልም በተለያዩ ክልሎች ከተሞች አዳዲስ ህንጻዎችን ለመገንበት ባንኩ በያዘው እቅድ መሰረት  ማለትም በአምቦ፣ በወሊሶ በአሶሳ፣ በቦንጋ፣ በቡራዩ፣ በቢሾፍቱና፣በየቡ ከተሞች ለሚገነቡ ህንጻዎቸዎች የአርክቴክቼራል ዲዛይን ስራ ተጠና ቋል፡፡ የደንበኞችን አገልግሎት ለማሟለት የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራትም የባንኩን ሰራተኞች አቅም ለመገንባት ሲባል በበጀት ዓመቱ በባንኩ የስልጠና ክፍል በአገር ውስጥና ከአገር ወጪም ስልጠናዎችን በተሳካ ሁኔታ ሰጥቷል፤እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 24-29/2023 ለላቀ ለደንበኞች እርካታ  እንተጋለን በሚል መርህ ቃል የደንበኞች ሳምንትን በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች እጅግ በደመቀ ሁኔታ ማክበር ተችሏል፡፡

የዛሬ 29 ዓመት ወደ ባንኪንግ ኢንዱስትሪው ቀድሞ በመግባት ፈር ቀዳጅ የሆነውና በአምስት ቅርንጫፎችና በ137 ሰራተኞች ስራውን የጀመረው አዋሽ ባንክ ዛሬ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፎችን የመከፈት ተግባርን አጠናክሮ በመቀጠል እ.ኤ.አ. እስከ ሰኔ 30 ቀን 2023 ድረስ የቅርንጫፎቹን ብዛት ከ875 በላይ፣ የሰራተኞቹ ብዛት ደግሞ ከ20 ሺህ በላይ አድርሷል፡፡

Dec 21, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
124.6101 127.1023
GBP
153.1919 156.2557
EUR
135.1144 137.8167
AED
30.7026 31.3167
SAR
30.0597 30.6609
CHF
135.4765 138.1860

Exchange Rate
Close