አዋሽ ባንክ ከያንጎ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
በስምምነቱ መሰረት ሁሉም የአዋሽ ባንክ ደንበኞች የያንጎ የሞባይል መተግበሪያን ተጠቅመው የጉዞ ጥሪ ሲያደርጉ Awash00 ፕሮሞ ኮድ በመጠቀም እና የክፍያ አማራጫቸውን አዋሽ ባንክ በማድረግ በአዋሽብር ፕሮ ክፍያቸውን ሲፈጽሙ፣ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ጉዞዎች ላይ የ15% ቅናሽ የሚያገኙ መሆኑ ተጠቁሟል።አዋሽ ባንክ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት በማድረግ በትብብር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
የታታሪዎቹ/ቀጠሌወን ውድድር የቴሌቪዥን ፕሮግራም ጥቆማ!
በጉጉት የሚጠበቀው የአዋሽ ባንክ ታታሪዎቹ/ቀጠሌወን የስራ ፈጠራ ውድድር ተወዳዳሪዎች የፈጠራ ሀሳቦቻቸውን የሚያቀርቡበትና የሚፋለሙበት መሰናዶ እሁድ ጥቅምት 24 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን እንዲሁም በተመሳሳይ ቀን ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በOBN ቴሌቪዥን መተላለፍ ይጀምራል። እንዳያመልጥዎ!አዋሽ ባንክ!
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
ግሎባል ፋይናንስ መጋዚን ለ31ኛ ጊዜ ዓመታዊ የዓለም እና የየአገሮች ምርጥ ባንኮች ምርጫን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በምርጫው ከተካተቱት 36 የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ከተመረጡት ባንኮች መካከል አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ብቸኛው ምርጥ ባንክ በመሆን በተከታታይ ለ3ኛ ጊዜ መመረጡ የሚታወስ ሲሆን፣ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ (WB) በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት የጋራ ጉባኤ ላይ የዕውቅና ሽልማቱን የባንካችን ዋና […]
የአዋሽ ባንክ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አረንገጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተካሄደ
የእህት ኩባንያዎቹ አዋሽ ባንክ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ሠራተኞች ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ምየ6ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ በአስኮ ብርጭቆ ፋብሪካ አካባቢ 20 ሺህ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ እህት ኩባንያዎቹ በኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት መርሐ ግብራቸው በስፋት ከሚሳተፉባቸው ተግባራት አንዱ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን መደገፍ ሲሆን በተለይ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ በሀገራችን የልማትና የምጣኔ ሀብት ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን […]
የ2023/24 የስራ አፈፃፀም ግምገማ
የአዋሽ ባንክ የሥራ አመራር አባላት ዓመታዊ ጉባኤ እ.ኤ.አ. የ2023/24 የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና የቀጣይ የስራ ዕቅድ አቅጣጫ ላይ ተመከሩ
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
አዋሽ ባንክ ከዓለም ምርጥ ባንኮች ውስጥ አንዱ ሆኖ ለሶስተኛ ጊዜ ተመረጠ! ግሎባል ፋይናንስ መጋዚን ለ31ኛ ጊዜ ዓመታዊ የዓለም እና የየአገሮች ምርጥ ባንኮችን ምርጫን ይፋ ባደረገው መሠረት በምርጫው ከተካተቱት 36 የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ከተመረጡት ምርጥ የአፍሪካ ባንኮች መካከል አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመሆን ለ3ኛ ጊዜ ተመረጠ፡፡እ.ኤ.አ. በ2024 ዓ.ም የተካሄደው ምርጫ ከ150 በላይ ባሉ አገራት የሚሠሩ […]