የቼክ ክፍያ ሂሳብ
የቼክ ክፍያ ሂሳብ አገልግሎት የተንቀሳቃሽና የቁጠባ ሂሳብን አጣምሮ የያዘ ነዉ፡፡
የቼክ ክፍያ ሂሳብ አጠቃቀምና ጠቀሜታዉ፡-
- የቁጠባ ሂሳቡንና የተንቀሳቃሽ ሂሳቡን አንድ ላይ ለማጣመር ደንበኛዉ ለባንኩ ማረጋገጫ መስጠት አለበት፤
- የተንቀሳቃሽ ሂሳቡ ወለድ የማያስገኝ ሲሆን የቁጠባ ሂሳቡ መደበኛዉን የወለድ ምጣኔ ያስገኛል፤
- የ3,000,000 ብር ተቀማጭነት መመዘኛ ተሟልቶ አስከተገኘ ድረስ የገንዘብ ወጪ ማድረጊያ ጊዜ ብዛት ገደብ አይኖረዉም፤
- ከተንቀሳቃሽ ሂሳብ ዉስጥ የተቀማጭ ገንዘብ ዕጥረት ሲያጋጥመዉ ደንበኛዉ ወዲያዉኑ የቁጠባ ሂሳቡን ማንቀሳቀስ ይችላል፡፡
የቼክ ክፍያ ሂሳብ ተጠቃሚዎች፡-
የቼክ ክፍያ ሂሳብ የተንቀሳቃሽና የቁጠባ ሂሳብን በአዋሽ ባንክ አጣምረዉ ለሚከፍቱ ደንበኞች የተዘጋጀ አገልግሎት ነዉ፡፡