አዋሽ ባንክ ዘመናዊ የዲጂታል ቅርንጫፎችን አገልግሎት አስጀመረ፡፡

አዋሽ ባንክ ጥቅምት 24 ፣ 2016 ዓ.ም (አዲስ አበባ)፣ ዘመናዊ እና አስተማማኝ የባንክ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለማቅረብ ሁሌ የሚተጋው አዋሽ ባንክ የዲጂታል ቅርንጫፍ (e-Branch) የማስጀመሪያ መርሐ-ግብርን በአዲስ አበባ ጌቱ ኮሜርሻል ሴንተር እና ብስራተ ገብርኤል አካባቢ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ውጪ በአዳማ ከተማ በይፋ በማስመርቅ አገልግሎት አስጀምሯል፡፡
ባንኩ ይፋ ያደረገው የዲጂታል ቅርንጫፎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ያሟሉ በመሆናቸው ደንበኞች ያለማንም ጣልቃ ገብነት በማንኛውም ጊዜ የሚፈልጉትን አገልግሎት እራሳቸውን በራሳቸው የማስተናገድ ዕድልን እንደሚፈጥር የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው በስነ-ስርዓቱ ላይ ገልፀዋል፡፡

Jan 15, 2025 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
124.7041 127.1982
GBP
153.3074 156.3736
EUR
135.2163 137.9206
AED
30.7258 31.3403
SAR
30.0824 30.6841
CHF
135.5787 138.2902