የእህት ኩባንያዎቹ አዋሽ ባንክ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ሠራተኞች ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም
የ6ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ በአስኮ ብርጭቆ ፋብሪካ አካባቢ 20 ሺህ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ እህት ኩባንያዎቹ በኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት መርሐ ግብራቸው በስፋት ከሚሳተፉባቸው ተግባራት አንዱ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን መደገፍ ሲሆን በተለይ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ በሀገራችን የልማትና የምጣኔ ሀብት ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ካስቀመጡት የግል የፋይናንስ ተቋማት መካከል ግንባር ቀደም መሆናቸው ይታወቃል፡፡
አዋሽ ባንክ